በዳውሮ ዞን በትራፊክ አደጋ የ 2 ሰዎች ህይወት አለፈ
******************
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ሎማ ቦሳ ወረዳ ከገሣ ከተማ ወደ ሎማ ባሌ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዚ ተገልብጦ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በደረሰው አደጋ 10 መንገደኞች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሳባቸውም ተገልጿል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያ ወደሚገኙ የጤና ተቋማት ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
የአደጋዉን መንስኤ የትራፊክ ፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመልክቷል።