የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን አሸነፈ
*******************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ፤ የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ሁለት ሽልማቶችን አሸንፏል፡፡
አየር መንገዱ የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ ዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ በሚሉ ዘርፎች ነው የአቬሽን አቺቭመንት አዋርድን ያሸነፈው፡፡
ሽልማቶቹ አየር መንገዱ ለልህቀት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ሲሆን አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማሱን እያሰፋ መሄዱን ተከትሎ በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚያስችለውም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ “አሸናፊዎች እንድንሆን ላበቁን የምንጊዜም አጋሮቻችን እና ታታሪ ሰራተኞቻችን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን” ብሏል፡፡
አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡