የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከአሜሪካ ልዑክ ጋር ተወያየ
***************
የዓለም የንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከአሜሪካ ልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ውይይት አድርጓል።
የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።
ለአባልነቱ የሚደራደረው የኢትዮጵያ ቡድን በ5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ላይ ቡድን ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ በሁለተኛ ቀን ውሎው ከአሜሪካ ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርጓል።
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ቡድኑ ከአሜሪካ ልዑክ ጋር ያደረገው ውይይት በሁለትዮሽ የገበያ መዳረሻ ድርድር ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ወደ ፊት የገበያ ዕድሎችን ከማስፋት አንጻር በአገልግሎት፣ በግብርና እና ሌሎች ምርቶች የገበያ ዕድል ዙሪያ ከአሜሪካ በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ መሰጠቱን አመልክተዋል።
የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነት መርህ ተኮር ሆኖ በሚጠናከርበት አግባብ ላይ የጋራ ግንዛቤ መፈጠሩንም ተናግረዋል።
የዓለም የንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ትናንት ከአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጉ የሚታወስ ነው።