ሆሣዕና
ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲኾን ትርጉሙ
ማለት ነው። በዓለ ሆሣዕና ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓላት መካከል ነው። በዚህ ዕለት ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ጀርባ ሆኖ የገባበት፣ሕዝቡ ዘንበባ ይዘው የዘመሩበት፣ሕፃናት በንጹህ አንደበታቸው "ሆሣዕና በአርያም ለወልደ ዳዊት" እያሉ ያመሠገኑበት ዕለት ነው።
የዚህ ዕለት ዝርዝር ጉዳይ በወንጌል በጎላ ሁኔታ ተጽፎ እናገኘዋለን
“በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
3: ማንም አንዳች ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልጉታል፡ በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።”ማቴ 21:1
ሁለቱ የተላኩ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ናቸው። ሁለት መሆናቸው ለሕዝብና ለአሕዛብ ሐዋርያ አድርጓ እንደሚልካቸው ሲያጠይቅ ነው። የሚገርመው ነገር የሐዋርያቱ አላማጉረምረም ነው የሰው አህያ ለዚያው ከታሰረችበት አምጡ ሲባል እሺ በጎ ማለት ምን አይነት መታዘዝ ነው !
እኛስ እንኳን የሌላውን ንብረት በራሳችን ላይ እንኳን ያድር ዘንድ ፈቃደኛ ነን ?
የሆነውስ ሆነ ለምን ጌታ በሜዳ ያሉ፣ያልታሠሩ ብዙ አህዮች እያሉ የታሰረችው የሰው ንብረት የሆነችውን ፈለገ ? አበው በትውፊት ይህች አህያ ከነ ውርንጫዋ የተሰረቀች እንደሆነች ይናገራሉ !
ጌታ በፈሊጥ ለሐዋርያት ስራቸውን እየነገራቸው እና በተግባር እያሳያቸው ነው ይህም እንዲህ ነው ፦
የእናንተ መደበኛ ስራ እና ኃላፊነት የታሠሩትን መፍታት ፤ ሌቦች አጋንንት ልባቸው እየሰረቁ መንፈሳዊ ማንነታቸውን እያደቀቁ በኃጢአትና በክህደት ወደ አሰሯቸው ሰዎች ሄዶ ፈትቶ ማምጣት ነው ሲላቸው እንዲህ አደረገ !
የሰው ልጅ በዋናነት በሁለት አይነት ማዕሠር ይታሠራል እኒህም
1.የኃጢአት እስር
2.የክህደት እስር
ከነዚህ ማዕሠር ፈትቶ ማምጣት የካህናት፣የመምህራን ተቀዳሚ አገልግሎት ነው።
ለምን በአህያ ተቀመጠ ?
ሰማዩ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ለዘለዓለም አድሮ የሚኖር ዓለማትን ሁሉ የፈጠረ አኃዜ ዓለም በእራኁ የተባለ ጌታ በአህያ መቀመጡ ስለምን ነው ? ያውስ ቢሆን በክብር የላቁ የምድር ነገሥታታት በሚቀመጡባቸው በሠረገላ፣በፈረስ ስለምን አልተመጠም ቢሉ፦
ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው !
እነሆ ንጉሥሽ የባሕርይ አምላክ የዋህና ኅዳጌ በቀል ሆኖ በአህያ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ትን.ዘካ 9፥9 ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው።
ምሳሌው፦
በዘመነ ብሉይ ነቢያት ዘመኑ ሰላም አይደለም ለማለት በፈረስ ተቀምጠው ጥቁር ለብሰው ጥቁር ጠምጥመው ይታዩ ነበር።
በተመሳሳይ ዘመኑ ዘመነ ሰላም የዕርቅ ዘመን ነው ሲሉ በአህያ ላይ ተቀምጠው ነጭ ለብሰው ነጭ ጠምጥመው ነጭ መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበር።
እንዲህ እንደሆነ ሁሉ እንግዲህ ዘመኑ ሰላም ነው እኔ ከአብ ጋር አስታርቄችኋላሁ አትፍሩ ዲያቢሎስዐተወግዶ የአዳም ልጅ ነጻ ወጥቷል ለማለት ጌታ በአባቶቹ በነቢያት ልማድ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ አባቶቹ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አባቱ ቤት ቤተ መቅደስ በዚህ ዕለት ገብቷል።
ምሥጢሩ፦
በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም ርቆ አይሄድም እኔም ከአይሁድ አላመልጥም ምንም በጨለማ በሠራዊት ታጅባችሁ በተክል ቦታ እንደ ወንበዴ ልትይዙኝ ብትመጡም እኔ ግን በመካከላችሁ በደካማዋ ፍጥረት በአህያ ተጭኜ እመላለስ ነበር ሲል ነው።
አህያ ከጥንት እስከ ዛሬ እንደ አገልግሎቷ ያልተመሠገነች እንደሁም "ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ" እንዲሉ ምስጋናው ቀርቶባት ዱላው የበረታባት ፣ ጀርባዋ በሸክም ብዛት ያበጠ የተላጠ ምስኪን ፍጥረት ናት አህያ !
ያም ብቻ አይደለም ስሟ ከፍጥረት መጠሪያ ላቅ ባለ ሁኔታ ለስድብ ያገለግላል አህያ !
ጌታ በዚች በተናቀች ፍጥረት ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ የገባው አይዟችሁ ምንም ብትናቁ ምንም ለ5500 ዘመን በዲያቢሎስ ሸክም ወገባችሁ ቢጎብጥ ጀርባችሁ ቢላጥ ከዚህ በኋላ የማንም አይደላችሁም የኔ ናችሁ፤ እኔ አድሬባችሁ እኖራለሁ ሲለን ነው !
ዘንባባ🌿🌿
1.ዘንባባ የደስታ ምልክት ነው በብሉይ ኪዳን የነበሩ አበዉ ደስታን ሲሰሙ ዘንባባ ይዘው ማመስገን ልማዳቸው ነው።
አብርሃም የተስፋ ልጁን ይስሐቅን በወለደ ጊዜ ደስ ቢለው የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ መሠዊያውን እየዞረ እግዚአብሔርን አመስግኗል ኩፋሌ 13፥6
2.ዘንባባ የድል ምልክት ነው በዘመነ መሳፍንት እስራኤልን ዮዲት ከሆርሆርኒስ ከሚባል ክፉ የአሕዛብ ንጉሥ ነጻ ብታወጣቸው ፳ኤላውያን ደስ ብሏቸው የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እግዚሔርንንና ዮዲትን አመሥግነዋል።
3.ዘንባባ እሾኻማ ነው ዙሪያው በእሾኽ የተከበበ ነው ይህም የጌታ ምሳሌ ነው ጌታ ሆይ ምንም ስጋ ብትለብስ በአህያ ጀርባ ተጭነህ ብትታይ አንተ ግን በዘባነ ኪሩብ ያለህ ባሕሪይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
4.ዘንባባ እሳት በቀላሉ አይበላውም የዚህ ምሳሌ ደግሞ መለኮት ከትስብእት ፤ ትስብእት ከመለኮት ያዋሐድክ እሳታዊ አምላክ ሥግው ቃል አንተ ነህ ነገር ግን ምን መለኮት ከሥጋ ፤ ሥጋ ከመለኮት ጋር ቢዋሐድ አምላክነትህ አልተለወጠም ሲሉ ነው።
5.የዘንባባ ፍሬ/ቴምር/ ጣፋጭ ነው ይህም የጌታ ምሳሌ ነው በአንደበት መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችንም የመረረ ሕይወታችንን ፣ የጎመዘዘ ኑሯችንን ሊያጣፍጥልን። ከመራራው ዲያቢሎስ ግዞቶ ነጻ ያወጣን ዘንድ መምጣቱን ያጠይቃል።
ሰሙነ ሕማማት የሚገባው እሁድ ጠዋት ጸሎተ ፍትሐት ከተከናወነ በኋላ ነው ሆሣዕና በኹለት ስሜት ይከበራል ከቅዳሜ ጀምር በደስታ እና ከእሑድ ቅዳሴ በኋላ በኅዘን።
ይህ የሚያስረዳው የአዳምን ኑሮ ነው አዳም ዕጸ በለስን ከመብላቱ በፊት የነበረውን ደስታ እና ከበላ በኋላ የወደቀውን ውደቀት እንደ የደረሰበትን ኃዘን።
መ/ር ነቢዩ ኤልያስ
👉ለመማር:https://t.me/Ze_Wengel
👉ቻናሉ:https://t.me/Terha_Tsion
ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲኾን ትርጉሙ
አቤቱ አሁን አድን