👉የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተሰጠ
የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ በፊት እንዲጠናቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሀመድና የግንባታው ተቋራጭ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የብሔራዊ ስታዲዮም የግንባታ ሂደት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ዛሬ ተካሄዷል።
በግምገማው አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በስታዲየሙን አሁናዊ ግንባታ ሁኔታም ምልከታ ተደርጓል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ብሔራዊ ስታዲየሙ ከተያዘለት ጊዜ በፊት መጠናቀቅ እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ተቋራጩ በበኩሉ ለስታዲየሙ ቀሪ ሥራዎች የሚሆኑ ግብዓቶችን በማስገባት ላይ እንደሆነ ገልጾ፣ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ለማፋጠን እንደሚሠራ መግለጹን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@etconp