👉የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች
🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።
ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።
⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።
[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል
[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ
[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት
[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ
[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ
[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።
[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡- ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል
[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት
[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል
[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ - 𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦ የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ
[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦ በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር
🔰እነዚህ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በዝርዝር እና በጥልቀት ይዘው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል።
@etconp