👉በጎረቤት መሬት ውስጥ ወሰን አልፎ ግንባታ ስለመፈጸም -- (የሕግ አግባብ)
🚧ከግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ በሀገራችን ፍርድ ቤቶች ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ሰፊውን ቦታ የያዘው «ጎረቤት ወሰን አልፎ አጥር ማጠር፣ እጽዋት መትከል እና በመሬት ውስጥ ወይም በአየር ላይ ግንባታ መፈጸም» በሚሉ ጉዳዮች የቀረቡ አቤቱታዎች ናቸው።
⏺በመሆኑም አንድ ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ከተሰጠበት የይዞታ ድንበር መስመሮች ውጪ በመሬት ውስጥም ይሁን ከመሬት በላይ (በአየር ላይ አንጠልጥሎ) ግንባታ መፈጸም አይችልም።
⏺ግንባታ ይቅርና ባለይዞታው ካልፈቀደ በቀር እና በህግ ትእዛዝ ካልተሰጠ በቀር ማንም ሰው በሌላ ይዞታ ላይ አልፎ መግባት (መራመድ፣ መቆም) አይችልም (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1216)።
⏺አንድ ጎረቤት በራሱ ይዞታ ላይ ዛፍ ቢተክልና ዛፉ እያደገ ሲሄድ የዛፉ ሥሮች በመሬት ውስጥ ወደሌላኛው ባለይዞታ መሬት ውስጥ ቢገቡ አልፈው የገቡትን የዛፉን ሥሮች የመቁረጥ ግዴታ አለበት፣ የዛፉ ቅርንጫፎችም በአየር ላይ በሰው ይዞታ ላይ ከገቡ ወይም ቅርንጫፎቹ ወደሌላ ጎረቤት ይዞታ ውስጥ ከተስፋፉ እነዚያን ቅርንጫፎች የመቁረጥ ግዴታ አለበት (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1212)
📜በመሆኑም በፍትሐብሔር ህግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድ ሰው በጎረቤቱ ይዞታ ላይ ግንባታ የፈጸመ ከሆነ (በመሬት ውስጥ መሰረት ግንባታ Foundation፣ በመሬት ላይ ወለል ወይም በአየር ላይ ተንጠልጣይ ውቅር Cantliver Structure ሊሆን ይችላል) ይዞታ የተጣሰበት አካል የባለቤትነት አቤቱታ በፍትሐ ብሔር /ሕ/ቁ 1206 መሰረት በማዘጋጀት ስልጣን ላለው ፍ/ቤት የማመልከት መብት አለው፡፡
⏺አቤቱታው ይዞታው በሚገኝበት አካባቢ ባለ ፍርድ ቤት ቢሆን የተመረጠ ሲሆን በይዘት ደረጃ የይዞታው ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የተያያዘበት፣ ግንባታ የፈጸመው አካል ምን ያህል ካሬሜትር አልፎ እንደገባ፣ እና ያለአግባብ የተፈጸመውን የግንባታ አይነት በመጥቀስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
⏺የአቤቱታው ፍሬ ነገር (ፍላጎት ደግሞ) ግንባታ የፈጸመው አካል አልፎ የገነባውን የግንባታ አይነት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታውን ቀድሞ በነበረበት ይዘት እንዲያስረክብ ውሳኔ እንዲወሰን የሚጠይቅ መሆን አለበት።
⭐️የቴግራም ቻናላችን፦ t.me/ETCONpWORK
ቴሌግራም ሊጽፉልን ካሰቡ፦ t.me/ETCONpBOT
💫የ FACEBOOK ገፃችንም ይወዳጁ👇
https://www.facebook.com/ethioconp
@etconp