👉የሐምዛ ድልድይ ግንባታ በመከናወን ላይ ነው
🚧በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ከጦር ኃይሎች አደባባይ ወደ የሺ ደበሌ በሚወስደው መንገድ በሚገኘውና በሐምዛ መስጊድ አካባቢ የሚገኘው የድልድይ ግንባታ በመከናወን ላይ ነው፡፡
💫በአካባቢው የሚገኘው የማህበረሰብ ክፍል ከዋናው የአስፋልት መንገድ ጋር የሚያገናኝ ምንም ዓይነት መንገድ ባለመኖሩ በአካባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
⏺ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አሁን ላይ ይህንን ችግር ለመፍታት በራስ ኃይል እየገነባው የሚገኘው የሀምዛ ድልድይ ግንባታ የመቃረቢያ መንገድ ጨምሮ 100 ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው፡፡
⏺ከዚህ በተጨማሪም 180 ሜትር ርዝመት ያለው የድጋፍ ግንብ ግንባታ፣ የሰቤዝ እና የገረጋንቲ ሙሌት ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡
⏺አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ ፊዚካል አፈፃፀም 60 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
Via የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
@etconp