👉ይርጋለም ኮንስትራክሽን በ4.8 ቢሊዮን ብር የፊደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንፃን ሊገነባ ነው
የፊደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ4.8 ቢሊዮን ብር ህንፃ ለማስገንባት ከከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራሟል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፤ በ4.8 ቢሊዮን ብር የህንፃ ግንባታ ስምምነት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለቤትነት በይርጋዓለም ኮንስትራክሽን የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የህንጻው ግንባታ እስከ መስከረም 2019 ዓም ድረስ የሚጠናቀቅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ግዙፍና በሀገር ውስጥ ኮንትራክተር የሚተገበር መሆኑን ገልፀው፤ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዕድገት ማሳያና ማስቀጠያ ነው ብለዋል።
ስምምነቱ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው፤ የህንፃ ግንባታው የፍትህ አገልግሎትን በአንድ ማዕከል በመስጠት የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።
እንዲሁም ለዳኞች እና ድጋፍ ሰጪ የፍትህ ዘርፍ ሰራተኞች አመቺ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስች መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን በማካተት የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት ይረዳል ብለዋል።
Via EPA
@etconp