👉ከአያት ሪል ስቴት ሱቅ የገዙ ሰዎች በድርጅቱ ላይ አቤቱታ አሰሙ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አያት ሾፒንግ ሞል በሚል በተገነባው ህንፃ ውስጥ ሱቅ የገዙት የዛሬ 16 አመት እንደነበር አቤቱታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ ድርጅቱ በሁለት አመት ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ እንደሚያስረክባቸው ቃል እንደገባላቸውም አስረድተዋል፡፡
የአያት ሞል ሱቅ ባለቤቶች ማህበር ፀሀፊ ሩት ግርማይ ስትናገር ‹‹እኛ የማህበሩ አባላት በህጋዊ መንገድ ሱቅ የገዛንና ውል የፈፀምን ነን፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ተገቢውን መሰረተ ልማት አሟልቶ ባለማጠናቀቁ ሱቃችንን ለመረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናችን ተዘግቶ ይገኛል›› ብላለች፡፡ እንደገለፀችውም በህንፃው ውስጥ ካልተጠናቀቁት መሰረተ ልማቶች መካከል መብራት፣ ውሀ፣ መፀዳጃ ቤት፣ መኪና ማቆሚያና ሊፍት ይገኙበታል፡፡ የህንፃው ግንባታ ረጅም ጊዜ በመቆየቱ አንዳንድ የማህበሩ አባላት በራሳቸው ወጪ አጠናቀው ስራ መጀመራቸውን ሩት ገልፃለች፡፡
ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ለመውሰድ ቢፈልጉም የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው ጠቅሳም በአሁኑ ወቅት ለሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አቤቱታ በማቅረብ ላይ ቢሆኑም ምንም መፍትሄ አለማግኘታቸውን አስርታለች፡፡
የአያት ሪል ስቴት ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብይ ማሞ ስለጉዳዩ ከዘሪፖርተር ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹እኛ ሱቅ ገዢዎቹን በመነጋገርና በውይይት ችግሩን እንድንፈታ ጠይቀናቸው ነበር፡፡
እነሱ ግን ጉዳዩን ወደተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መውሰድን መርጠዋል›› ካሉ በኋላ ጉዳዩን ለመፍታት በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
Via ዘ-ሐበሻ
@etconp