👉የዲጂታል ካርታ ጥያቄ ያቀረቡ ተገልጋዮች ይዞታቸውን መነጠቃቸውን ተናገሩ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የዲጂታል ካርታ ጥያቄ ያቀረቡ ተገልጋዮች ይዞታቸው ለካራ ቆሬ አፓርታማ እንደተሰጠባቸው ተናገሩ።
ለመሠረት ሚዲያ አስተያየታቸውን የሰጡ ባለጉዳዮች እንዳሉት ለመኖሪያ ቤት የዲጂታል ካርታ ጥያቄ በኦላይን ካቀረቡና የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር በኩሉ እንዲከፍሉ ከተደረገ በኋላ የኦላይን አገልግሎቱ መቋረጡን እና ሰነዳችሁ አልተሟላም ተብለው በኦላይን መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለምን እንደተቋረጠባቸው ለመጠየቅ ወደ ክፍለ ከተማው ባቀኑበት ጊዜ ደግሞ ይዞታቸው ለካራ ቆሬ አፓርታማ እንደተሰጠባቸው በመሃንዲሶች በኩል መገለጹን እንደሰሙ አስረድተዋል።
"መፍትሄ የሚሰጠን አካል የለም" የሚሉት የክፍለ ከተማው የዲጂታል ካርታ ተገልጋዮች "ለበርካታ አመታት ለፍተን የሰራነውን ቤትና ይዞታ በቀላሉ ለካራ ቆሬ አፓርታማ ተሰጥቷል መባሉን አንቀበልም" ብለዋል።
Via Meseret Media
@etconp