👉የግንባታ ሠራተኞች ደኀንነትን በመጠበቅ የሚገኙ ትሩፋቶች
💫የኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች የሠራተኞቻቸውን ደኀንነት የመጠበቅ ግዴታን በተግባር ሲያረጋግጡ የሚያገኟቸው ትሩፋቶች በርካታ ናቸው፤ ከእዚህ ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
፩
ሠራተኞች ከሥራ ገበታ የሚቀሩበትን ድግግሞሽ ይቀነሳል
▪️
አንድ ሠራተኛ ሥራውን ሳያስተጓጉል በየዕለቱ በሥራው ገበታ ላይ ሊገኝ የሚችለው በአእምሮ ሆነ በተክለ ሰውነት ጤናማ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡
ሠራተኛው በሥራ ቦታ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የሚከላከልበት የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች እንዲሟሉለት በማድረግ፣ ከስጋት ተጠብቆ ሊንቀሳቀስበት የሚችልበትን መንገድ በማዘጋጀት፣ ፈጣን የሕክምና አገልግሎት የሚያገኝበትን አሠራር በመዘርጋት፣ ሠራተኛው ከሥራ ገበታ የሚቀርበትን ድግግሞሽ እንዳቀንስ እና በአግባቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
፪
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ይጨምራል
▪️
አንድ ሠራተኛ ሲታመም አስፈላጊን የሕክምና ድጋፍ በፍጥነት የሚያገኝ፣ አደጋ በደረሰበት ጊዜ ሞራሉን የሚጠብቅ ካሣ የሚያገኝ ከሆነ፣ ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሥራው ላይ ያደርጋል፡፡ ነገ አንድ አደጋ ወይም በሽታ ቢደርስብኝ ምን እሆናለሁ ከሚል ስጋት ይላቀቃል፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ ሠራተኛ በሥራው ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ ሲጀምር ለኩባንያው የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በተመሳሳይ ይጨምራል፡፡
፫
ሥራውን እንዳይለቅ የሚያደርግ መተማመኛ ይፈጠራል
▪️
አንድ የኮንስትራክሽን ካምፓኒ አስፈላጊውን ክህሎት የተላበሰ ባለሙያ እንደሚፈልግ ሁሉ፣ አንድ ባለሙያም በሙያው ከሚሰጠው አገልግልት ለዘላቂ ሕይወቱ ዋስትና የሚሆነውን ገቢ፣ ጥቅማጥቅም እና የአገልግልት ክፍያ ማግኘት ቀዳሚ ምርጫው ይሆናል፡፡
በተለያየ የሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ኤክስፐርቶች "The Scene of Happiness" በሚል ርዕስ ያቀረቡት የጥናት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አንድ 50 ሺህ ብር ቋሚ ደሞዝ ከሚያገኝ ሠራተኛ ይልቅ፣ በወር 1 ሺህ ብር እየተከፈለው በየዓመቱ የደሞዝ ጭማሪ የሚያገኝ ሠራተኛ የሚሰማው ደስታ ከፍተኛ ነው፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ዘግይቶ ከሚመጣ ከፍተኛ ገቢ ይልቅ፣ ከስር ከስር ተጨማሪ ገቢን ወይም ለውጥን ማየት ይፈልጋል፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የተሰማሩ ሠራተኞችም በየወሩ ከሚከፈላቸው ደሞዝ ባልተናነሰ፣ በየጊዜው በሚሰጣቸው ጥቅማ ጥቅሞች፣ ቦነሶችን ጨምሮ በመጨረሻም ከሥራው ጨርሰው ሲለቁ በሚያገኙት ካሣ እና ድጎማ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፤ ይህን ፍላጎት የሚያሟላ ካምፓኒ ካገኙ ደግሞ የሚያጓጓ ጥቅም (ደሞዝ) የሚያስገኝ የሥራ ጥያቄ ቢቀርብላቸው እንኳ፣ ሥራቸውን ለቀው ለመሄድ ፈቃደኛ አይሆኑም፡፡
፬
የካምፓኒውን ስም እና ዝና የጎላ ይሆናል
▪️
ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላቸው ድርጅቶች፣ ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት ደሞዝ፣ ሌሎች የተለያዩ ድርጅቶች ተመሳሳይ ሞያ ላላቸው ሠራተኞች ከሚከፍሉት ደሞዝ ብዙም ልዩነት ያለው አይደለም፡፡ እውነታው ከዚህ ወጪ ባይሆንም፣ ኩባንያዎች በባለሙያዎች ተፈላጊ እንዲሆኑ እና ዝናን እንዲላበሱ የሚያደርጋቸው ለሠራተኞቻቸው በሚሰጡት ድጎማ፣ የደህንነት ጥበቃ፣ ጉርሻ እና ካሣ ከፍተኛነት የተነሳ ነው፡፡ ሠራተኛው እነዚህን ከፍተኛ ጥቅማ ጥቅሞች የሚያገኘው ሥራውን በአግባቡ ሲወጣ እና ካምፓኒው ትርፋማ ከሆነ ብቻ መሆኑን በአግባቡ ስለሚረዳ፣ ለሥራው ያለው ጉጉት እና ተነሻሽነት ከፍተኛ ይሆናል፡፡
@etconp