ህልም እልም
"በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ"
"ምነው?" ሚስት መብራት አበራች
"ሰው ገደልኩ"
"መቼ?"
"አሁን በህልሜ…አንቺን ሲነኩብኝ አልወድ፣ ምን እንደፈረደበት እንጃ ይሄ ጎረቤታችን ጎሹ ሲስምሽ የደረስኩኝ ይመስለኛል።
ከራስጌ ቆንጨራዬን መዘዝ ሳደርግ ያ ዲብ ሰውነቱ'ኳ ሳይከብደው ፈትለክ ይላል። ሲበር፣ ሳባርር…ሲበር ሳባርር ጎሹ እንዴት እንደሆነ እንጃ እየራቀኝ ይሄዳል።
ቆንጨራውን እንደቅዝምዝም ሃይ ብዬ ስወረውረው ጀርባው ላይ ስክት ሲል ብንን አልኩ። በስመ አብ ወወ…"
"ህልም አይደለም!"
"እ"
"አዎ እውነት ነው። ትናንት ጎሹ መሳም ስሞኛል፣ ግን አላባረርከውም፣ ዝም ብለህ ነው ያየኸው?"
"ነው እንዴ? ነፍስ ከማጥፋት እግዜር አወጣህ በይኛ"
,,,ውልብታ,,,
#ዓለማየሁ_ገላጋይ