እሁድ ጠዋት ነው ከተዘረሩበት ሜዳ
ላይ የባጥ የቆጡን ሲያነሱ ሲጥሉ ቆይተው ገና ዝም ከማለታቸው ክንዱን ተንተርሳ ከተጋደመችበት ቀና ሳትል "አይገርምም?!" አለች ቅሬታ ያዘለ ፈገግታ ፈገግ ብላ
እንደዚህ በመሀል እንደቀልድ ያወራችው እንኳን ከውስጡ ስለማይጠፋ ሰፍ ብሎ "ምኑ"
"ትዝ ይልሀል ባለፈው ቁጭ ብለን ያሳለፍናቸውን ጥቃቅን ነገሮች እያነሳን በትዝታ ፈረስ ስንጋልብ..."
"አልረሳሁትም"
"ከዛ ምን እንዳልከኝ ታስታውሳለህ? እነዛ ጥቃቅን ነገሮች ያደረግንባቸው ቀናት ምናለበት እንደዚህ ቆንጆ ትዝታ እንደሚሆኑ ብናውቅ ኖሮ ይበልጥ ጥሩ ይሆን ነበረ ብለኸኝ ነበረ
ከዛ ግን አሁን እዚህ መቀመጣችን የሳሩ እርጥበት የፀሀይዋ ለስላሳ ሙቀት የምናወራው ወሬ ምናምን ቆንጆ ትዝታ እንደሚሆኑ ሳስብ ምን እንደተሰማኝ ታውቃለህ?"
"ምን ተሰማሽ?" ፊቷ ሲዳምን ያየ መሰለው
"እኔንጃ...ግን ደስ አላለኝም ስታስበው ትዝታ ምኑ ደስ ይላል?!" አለችው መከፋቷ እያስታወቀባት
"ነይ... ነይ... እስኪ" ብሎ እቅፉ ውስጥ ከቶ አንሾካሾከላት
"ለትዝታዎቼማ ብቻሽን አልተውሽም... የኔን ትዝታ መሆን መፍራት እስክታቆሚ ድረስ አብሬሽ ሆኜ ብዙ...ብዙ ቆንጆ ጊዜ ታሳልፊያለሽ
ሁሉንም ቀን እንደ አዲስ እየኖርን ትዝታን አቅም እናሳጣዋለን እሺ"
"እሺ"
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss