የምሽት ጎዳናዎች ጓደኛ አደረገን
አጠገባችን ለረጅም ዓመታት አብረውን ካሳለፉት በላይ አንዳንድ የመንገድ ጉዞዎች የተሻለ ቁርኝነትን ይፈጥራሉ። አንድ ቀን ነው ጥቂት ወሬዎች ነገር ግን ትልቅና አስገራሚ ትዝታዎች። አዎን ያልታሰቡ ሰዎች የምንኘውን እርካታ ይሰጣሉ። ታድያ ግን ቅጽበት ነው። በለኮስነው የክብሪት እንጨት ላይ ያለህ እድሜን ይወክላል፤ ያም አንዴ በርቶ መላ ጨለማውን ያስታቅፋል። ድንገታዊ ብልጭታ ነው በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያልበራ የልደት ሻማ።
በስኒ የተሞላው ቡና አቦልነቱ ሳይበርድ ወደ ጉሮሮ ሲንቆረቆር ወጣትነት ይባላል። ወጣትነት ትንሽ ነው እንደልጅነትና ሽምግልና አይንቀራፈፍም። ሲመጣ አይታወቅም ሲሄድም አናስተውለውም ነገር ግን ረጅም ታሪክ በውስጡ ተሸክሟል።