✨አቅም አሳጣቺኝ✨
ገና ከመረፋፈዱ አይኑን እያሻሸ መጥቶ የብፌውን በር በሀይል በርግዶ ራሱ ያጋመሰውን የውስኪ ጠርሙስ አውጥቶ መልሶ ደርግሞ ዘጋው።
"ተው እንጂ በመከራ የተሰበሰበውን ትኩረቴን የውስኪ ጠርሙስ በማውጣት ሰበብ ባትበታትነው?! ደሞ ሴትዮህ ናት እንጂ ብፌው ምን አደረገህ?!" አልኩ ታላቅ እህትነቴ በሚሰጠኝ ስልጣን
"ኤልዳና!" በሙሉ ስሜ የሚጠራኝ የእውነት ሲናደድ ስለሆነ ስመሰጥበት የነበረውን መፅሀፍ ዘግቼ "ምንድነው ደግሞ የሆንከው? ደግሞ ምን አደረገች" አልኩት ከተወሰኑ ወራት ጀምሮ ከሙሉ አለም በላይ የእሷ ነገር ብቻ ስለሆነ የሚያቃውሰው ብዬ ነው
"አዘዘችበት... ጭንቅላቴን አዘዘችበት አቅም አሳጣቺኝ" አለ ውስኪውን በጠርሙሱ እያንቆረቆረው።እንደዚህ ሲል የሜሪ ፈለቀን አዲስን ያስታውሰኛል
ውስኪው ጉሮሮውን ቅጥል ሲያደርገው ፊቱን ቅጭም እያደረገ ሲያስተናግደው ፈገግ አስባለኝ። 'ሰው ለምን ገንዘብ አውጥቶ ይጠጣል?' እያልኩ ዘወትር የሚደንቀኝን ነገር መልስ አገኘሁለት ግልፅ አይደለ?! ውስጣቸው ልባቸው ከሚቃጠል አካላቸው ጉሮሯቸው ምናምን ቢቃጠል ስለሚመርጡ እኮ ነው
"ምን አደረገች"
ሲናደድ እየተንጎራደደ መደስኮር ስለሚወድ የተፈጠረውን ከመስማቴ በፊት ትንሽ ዲስኩር መታገስ አለብኝ
"የሆነ ሰው ከዚህ በፊት ምን ብሎኝ ነበረ መሰለሽ አለምን የሚመራው control ነው ብሎኝ ነበረ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ ይሄንን የውስኪ ጠርሙስ ክዳን ባሽከረክረው ይከፈታል ግን ባስቀምጠው አርፎ ይቀመጣል ግን ሳስቀምጠው አርፎ አልቀመጥ ቢል እንዴት ሊያናድድ እንደሚችል አስበሽዋል?"
"አዎ ልክ ነህ ግን ይሄ ከእሷ ጋር በምን እንደሚገናኝ አልገባኝም"
"ግልፅ እኮ ነው ሁሉንም ነገር መቆጣጠር ችለሽ እንኳን መቆጣጠር የማትችይው ሰዎችን ነው አርቀሻቸው እንኳን ስሜትሽን ጭንቅላትሽን ሲያዙበት አቅም ያሳጣል አይደል?! ምን ማድረግ ትችያለሽ" አለ ሶፋው ላይ ዘፍ ብሎ ተቀምጦ
"ዛሬ ምን አድርጋ እንደሆነ እስካሁን አልነገርከኝም እኮ"
"በህልሜ አየኋት!!"
ግንባሩን በመዳፉ እየጠፈጠፈ "ወይኔ ሳዶር ወይኔ ወንዱ ናፍቀሽኛል አልኳት እኮ... ምን እንደሚያናድድ ታውቂያለሽ?!"
"ምን" አልኩት ሳቄን ዋጥ አድርጌ
"በህልም እንኳን... ያውም በራሴ ህልም እንኳን አትስትም እኮ "እኔ ግን አልናፈቅከኝም" አለቺኝ እሺ እኔ የት ልድረስ?! አላገኛትም አላያትም ብዬ ውሎዬን ቀየርኩ እሺ በህልሜም በሰላምም አልተኛ"
ከዛ በላይ ሳቄን መያዝ አልቻልኩ
"አይይ ሳዲቲ
'ደግሞ እንድነቃ ዳግም ቆሜ
አትመላለሽ መጥተሽ በህልሜ
የቀኑ ማማር ይበቃሻል
ከተኛው ቀልቤ ምን ቀርቶሻል'
የሚለውን የቴዲን ዘፈን ጋብዛት እሺ" እያልኩ ሳቄን አስነካሁት
"የኔን ይስጥሽ ምንም አልልም" ብሎ ውስኪውን ይዞ ሄደ
✍ናኒ
https://t.me/justhoughtsss