"ነይ ብለህ ነይ ብለህ "
አለማመኔን በዝግታ አሽቀንጥረህ ጥለህ ፣ ቁጥብነቴን ካባረርከው በኋላ ፣ በየወሬዎቼ ፣ በየህልሞቼ ፣ እንቅስቄሴ ውስጥ ተሰንቅረህ ከገባህ በኋላ ወዴት ሄድክ ??
ከለመድኩህ ፣ ካንተ ጋ ማርጀት ከሻትኩ በኋላ ፣ ሁሉ ነገርህን ሁሉ ነገሬ ከተቀበለ በኋላ ፣ የመጣሁበትን የምሄድበትን መንገድ ካሳየሁህ በኋላ ።
ጓደኛህ ፣ አማካሪዬ ፣ ውሎዬ
ከሆንክ በኋላ የት እየሄድክ ነው ?!
አልገባህም መሰል ልቤ ላይ እንዴት እንደተንጋለልክ ፣ አይኔ ፣ ጆሮዬ ፣ ቀልቤ ፣ ደመነፍሴ ለአንተ እንደሚያደላ
ለእኔ መቀበል እንደመተው ቀላል ይሆንልኝ መስሎህ ይሆን ?
ቶሎ ቶሎ ማፍቀር ፣ መቅረብ ፣ ማመን ፣ መርሳት እንደማይሆንልኝ ታውቅ የለ ?!
ተው አትጨክንብኝ... ታውቀኝ'የለ?