✅መስፈርቷ
ልጅ እያለሁ አብረን መርካቶ ያደግን ታየች የምትባል የልብ ጓደኛ ነበረችኝ። የሆነ ጊዜ ላይ ራጉኤል ጋር የነበረው የአባቷ ጨርቃ ጨርቅ ሱቅ በጣም ታዋቂ ሆነ። ከዛ ብዙም ሳይቆይ አለፈላቸውና መርካቶን ለቀው ኦልድ ኤርፖርት የሚባል ሰፈር ቤት ሰርተው ገቡ። እኔ እዛው መርካቶ ጭቃ ላይ እየተራገጥኩ አንበጣ ሳባርር ታየች ቢኪኒ የሚባል ጡት ማስያዣ ተገዝቶላት መዋኝት ተማረች። አልፎ አልፎ ቤታቸው ስጋበዝ ምቾቷ ይጋባል። የእማማ ራድያ የሽንት ቤት ፍሳሽ በግቢዬ የሚያልፈው እኔ፣ የእነ ታየች ግቢ ውስጥ ያለው ጋርደን ላይ ተንጋልዬ መጽሐፍ እያነበብኩ ስታይ፣ አይ ውበት። አመሻሽ ላይ ወደ መርኬ ለመመለስ ገብሬል ጋር ያለው ታክሲ ውስጥ ስገባ፣ መጽሐፌን ጭብጥ እድርጌ ይዤ ከስፊው ህዝብ ጋር ስገፋፋ፣ ጎበዝ ለካስ ምቾት ይተንናል!።
ጥቂት አመታት አልፈው እኔ በ"ክልክል" አጥር ውስጥ፣ ፍቅርኛ መያዝ በማይፈቀድልኝ አስተዳደግ ውስጥ ስዳክር ታየች ሳምሶን የሚባል እንደሷ
በምቾት የሚንሳፈፍ የከንፈር ወዳጅ ያዘች። ህልምና መጽሐፍን የሰጠኝ እግዚያር ግን ደግ ነው። አሁን ደሞ ቸርነቱ በዝቶ የእኔ ከንፈር እንኳ በእውን ባይሳም የጓደኛዬ የታየች ከንፍር ሲሳም ሊያሳየኝ! እሱ ምን ይሳነዋል!
አንድ ቅዳሜ ታየች ደወልችልኝና ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ሰነዘርች። "ቲጂዬ ዋና ትችያለሽ?".. ከሳምሶን ጋር ጊዮን ሆቴል ሊዋኙ ተቀጣጥረው ኖሮ አብሬያቸው እንድዝናና መጋበዝዋ ነበር። ምቾቷ አሳውሯት ነው እንጂ የት ነው እኔ መርካቶ ውስጥ ዋና የምማረው? ታደለች የምትቸረችረው የከሰል ሐይቅ ውስጥ? ወይስ ወ/ሮ የሻረግ ጠላ ቤት ያለው ማሰሮ ውስጥ? ታየች ፌዝ ተማረች። ታየች ዋና ተማረች። ከመርካቶ ቦይ በኮንጎ ጫማ ተንደርድራ በቢኪኒ ጊዮን ሆቴል የውሃ ገንዳ ውስጥ ተጠመቀች።
እሁድ ጠዋት የከንፈር ወዳጆቹን አጅቤ እነሱ ሊዋኙ እኔ ፎጣ ልጠብቅ ጊዮን ሆቴል ደረስን። ጁስና ኬክ ታዞልኝ እነሱ ውሃ ውስጥ ሲንሳፈፉ እኔ በእነሱ አለም ውስጥ ስንሳፈፍ፣ እንሱ በአራት ነጥብ የታጠሩ ደማቅ አርፍተ ነገሮች። እኔ ገና ያልተብራራው ተከፍቶ ያልተዘጋ ቅንፍ። ውሃ ሲረጫጩ ደስ ሲሉ። ይጎነታተላሉ። ኦ ቢኪኒዋ! አረንጓዴ ባለአበባ። ሳምሶን ከጀርባዋ ቆሞ እሷ ጸጉሯን ወደ ላይ ሰብስባ የላላውን የብኪኒዋን ገመድ እያሰረላት ሲጠጋት እሷ እየሳቀች ከወሲብ እንፋሎቱ ስትሸሽ። ሲያስቀኑ። በቀረብልኝ በጥቂት ደቂቃዎች ነው ኬኩንም ጁሱንም የሰለቀጥኩት። እንዲህ ያለው ምግብ በነጻ ሲገኝ ሰጪው ሃሳቡን ሳይቀይር ቶሎ ማውደሙ ከልምድ የመጣ ነው። የመርካቶ ቅደም ተከተሉ መጀመርያ ረሃብ ማስታገስ ከዛ ስለ ታየች የከንፈር ዕጣ ፈንታ ማሰላሰል።
በጨረፍታ እያየኋቸው ደስታቸው ተጋባብኝ። ያሽካካሉ። ፊታቸው ያብረቀርቃል። ሳምሶን ብዙ ሳምሶኖች ቢሆን፣ እኔን ጎትቶ ውሃ ውስጥ የሚያጠልቀኝ ሌላ ሳምሶን ከዚህኛው ላይ ተቆርሶ ቢመጣ። ሮዝ ቢኪኒ ቢኖረኝ። የቢኪኒዬ ገመድ ቢላላ፣ ሳምሶን ሊያስርልኝ ቢጠጋኝ፣ በወሲብ እንፋሎቱ እጠመቅ ነበር። መጣበቅ፣ መጠመቅ፣ አንድ መሆን። ታየች ለምን ሸሸች?
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ያላሰብኩት ክስተት ተፈጠረ። ታየች እየተጣደፈች ከገንዳው ስትወጣ አየኋት። ፊቷ ላይ ብስጭቷ ይነበባል። ዞር ብዬ ሳምሶንን ቃኝሁት። ግራ ገብቶት ፈዞ ያያታል። አጠገቤ ስትደርስ በፍጥነት ፎጣዋን አንስታ ገላዋን እያደራረቀች "ቲጂ ቶሎ መሄድ አለብን ተነሽ" ብላኝ ሳትጠብቀኝ ወደ ልብስ መቀየሪያው ክፍል አመራች። "ይህ ቀዥቃዣ ወሲባም ምን አድርጓት ይሆን?" ብዬ እያሰላሰልኩ ተከተልኳት። ለባብሳ ወደ ታክሲ ስናመራ የሳምሶን አብሮን አለመሆን ግራ እንደገባኝ ስታውቅ "የኔ እና የእርሱ ነገር አብቅቷል" ብላ በረጅሙ ተነፈሰች።
እንዴ? ይህ የተመቸው ቦንቦሊኖ የመሰለ ልጅ፣ ለመላው የመርካቶ ኮረዳ ኬክና ጁስ የመግዛት አቅም ያለው ሳቂታው የሃብታም ልጅ፣ ቢኪኒዋን ወሲብ በተሞላበት ርህራሔ ያሰረላት ስሱ ሳምሶን ምን አድርጓት ይሆን? ልምድ ያካበቱ የሚመስሉ ከንፈሮች እንዲሁ በዋዛ ሊቀሩ?
"ምን እንዳደረገ ታውቂያለሽ?" አለች እየተብከነከነች። "የውሃው ገንዳ ውስጥ፣ እዛ የምንዋኝበት ገንዳ ውስጥ፣ አፍንጫውን ጨምቆ፣ በሃይል እንፍፍፍፍፍ ብሎ ንፍጡን ስቦ ካወጣ በኋላ እዛው ውሃ ውስጥ አይወረውረው መሰለሽ? ከዛ ደሞ እጁን መለቃለቁ! አይኑን ማየት አልፈልግም" ብላ አስረግጣ ነገረችኝ።
✅ ወንድሜ ሆይ፣ የታየች መስፈርት ግልጽ ነው። መርሴዲስ ቢኖርህ፣ ተጫዋች፣ አማላይ፣ ሳቂታ አፍቃሪ ብትሆን፣ ነገር ግን ንፍጥህን በየቦታው የምታዝረከርክ ከሆነ፣ ከታየች ጋር እድል አይኖርህም። የህዋ ተመርማሪ ብትሆን፣ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ብትሆን፣ ምን አለፋህ የሮም ከተማን የቆረቆርከው መሃንዲስ አንተ ብትሆን፣ ግን ህዝብ የሚዋኝበትን የውሃ ገንዳ በንፍጥህ የምትበክል ዝርክርክ ከሆንክ የታየች አጸያየፍ ከእግዚያር ፍጥረት ሁሉ የረቀቀ ነው።
ትግስት ሳሙኤል