#5
"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት"......አልኳቸው...
ከዶርም ልጆች ጋር "ረጅም ጊዜ እምነታችንን ያገኙ ግን ደሞ ውሸት የነበሩ ነገሮች" በሚል ርዕስ ዙሪያ ያጋጠመንን በየተራ ለመናገር ተስማምተን ንግግሩ ከኔ ተጀምሮ ነው.....
ከሴት ጋር አንድ አልጋ ውስጥ አጊንቼው እህቴ ናት ቢለኝ አምነው ነበር....ቤቲ ደውላ፣ ኮኪ ጠርታኝ፣ ማሂ ፈልጋኝ እያለ የሴት ስም በዝርዝር ሲጠራልኝ በአንዲቷም እንደማይቀይረኝ በሰአቱ ፍቅሩ አረጋግጦልኛል.....
የhighschool የመጀመሪያ አመት ተማሪ እያለን ነበር ፍቅሩን መግለፅ የጀመረው....ከረጅም የእንቢታ ጊዜ በኋላ በሀሳቡ ተስማማሁ።
የሌላ ፆታ ፍቅርን ሀ ብዬ የተማርኩት በሱ ነው....ወንድሜ፣ ጓደኛዬ፣ ሚስጥረኛዬ እና ወደፊቴን አቃጄ ሆነ....24 ሰአት ልቡ እኔ ጋ ነበር....ታጋሽ፣ ትሁት፣ እኔን ደሞ እንደትልቅ ሰው አክባሪ ለኔ ከሱ በላይ አልነበረም። እኔም ፀሎቴ ውስጥ ሳይቀር ቅድሚያ ተሰላፊ አደረኩት
የህይወታችን ወሳኙ እድሜ ፣ አዲስ ነገር ሁሉ ሚፈጠርበት እድሜ ላይ ተገናኘንና አብሮነታችን ላይ ጥገኛ ሆንን....
ለፍቅር ያለኝ ትርጉም በዚ ግንኙነት ተመሰረተ....ማንም ፍቅረኛውን ወዶና መርጦ ካገባ በኋላ ሊከዳት ወይም ልትከዳው አትችልም, መጀመሪያም ያላፈቀረው ጋር ካልተጣመረ በቀር.....
ኮካዬን ጎንጨት ብዬ ወሬዬኔ ቀጠልኩ...
የሆነ ቀን እንደለመድነው ፍቅርሽን ለምን አትገልጪም በሚል ተጣልተን ሁለት ወይም ሶስት ቀን ተኮራረፍን( እውነቱን ነው ፍቅርን በቃል መግለፅ ላይ ጎበዝ አደለሁም😁...ተደጋጋሚ የመጣያ ርዕሳችን ነበር)።
ከዛም በሶስተኛው ቀን እንደለመድነው ብዙ አመት ተለያይቶ እንደቆየ ሰው ስናወራ ዋልን። በዙሪያ ያሉት ጎደኞቼ ሁሉ በኛ የ24 ሰአት ወሬ እንደተማረሩ ነው...ከልጅነት እስከ እውቀት ምታወሩት አያልቅባችሁም? የሁሉም ጥያቄ ነበር
መጨረሻ ላይም ያስጨነቀው ጉዳይ እንዳለና ልነግርሽ ፈልጋለሁ አለኝ...ህመሙና ጭንቀቱን ሳልሰማው ቢያልፍ ደስታዬ....ብዙጊዜ የሱን ችግር ሰምቼ እኔ እየታመምኩ ለሱም ፈተና ሁኜበታለሁ..... ምነው አልኩት
እንደቀላል ነገር በተደጋጋሚ ስሟን ይጠራው የነበረችው ልጅ ከሱ አረገዝኩ እንዳለችና እንዴት ልጁን እንደሚያሳድግ እንዳማክረው ጠየቀኝ.....ግራ ገባኝ...ለሱ የሴትነት ልኩ እኔ ነበረኩ....እህቱም፣ እናቱም፣ ፍቅረኛውም.....ምንም አላልኩም "እኔስ" ብቻ ነበር ያወጣሁት ቃል....
እሱም, በፈለገው ጊዜ በአካል ስለማያገኘኝ እና ፍቅሬን ስለማልገፅ
በፍቅር ቃል ልቡን እንዳሸፈተችና ሁሌም አጠገቡ እንደነበረች ነገረኝ( እኔ የት ሂጄ ማለት ፈልጌ ስላልቻልኩ ዝም አልኩ).....እንደሰው በክብር ተጣልተን ቢሆን ለዚ የበቃነው ደስ ባለኝ ....የሱ እርጋታ ደሞ እኔን እብድ ሊያደርገኝ ደረሰ....
እንደምንም እራሴን አረጋግቼ "መቼ ነው ኢኼ የሆነው" አልኩት... የሆነ የተለመደው ፀባችን ምሽት ላይ ከቆንጆ ወይን ጋር አጠገቡ ያገኛት እሷን ስለሆነ የኔ ክፍተት እንደሆነ በድጋሜ ነገረኝ....ሶስት ቀን ራሴን ታመምኩ
የቱ ጋር ፍዝዝ ብዬ እንደሆነ አላቅም አንቺ ጋ ነኝ እያለ እሷ ጋር የተገኘው.....
ኢኸው በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት.....በርግጥ የትኛው እምነቴ እንደተሳሳተ አላረጋገጥኩም..... "የእውነት አፍቃሪ ሊክድ አይችልም" ያልኩት ወይስ "እሱን እራሴን ከማምነው በላይ ማመኔ"....
ቶሎ ለመፅናናቴ ትልቁን ቦታ የወሰደው ግን ኢኼ ፅሁፍ ነው "ታምኖ የተገኘ ብቻ ሳይሆን አምኖ የተገኘንም ፈጣሪ ይክሳል" ....ብዬ ታሪኬን ጨረስኩ
ሁሉም አሳዘንኳቸው መሰለኝ ዝም ብለው ቀሩ
✍ሚሚ
https://t.me/justhoughtsss