ክፍል ፪
ውድ የ አሐቲ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻችን ፣ እንደምን አላችሁ! ዛሬ ደግሞ እያንዳንዳችንን ክርስቲያኖች የሚመለከቱ ሥርዓቶችን እንመለከታለን። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደመሆኗ ሥርዓት እንዳላት ሁሉ፣ እያንዳንዱ ክርስቲያንም የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደመሆኑ ሥርዓት አለው።
1. ለክርስቲያኖች የተሠሩ ሥርዓቶች
ቅዱስ ቃሉ ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አገልጋይ እንዲሁም ምእመን ሥርዓትን አስቀምጧል። ከእነዚህም መካከል፦
• ለጳጳሳት፡- ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ መሆን፣ ማየትና መስማት የተሳናቸው ወይም ጋኔን ያደረባቸው አለመሆን፣ ምሥጢራተ መጻሕፍትን ማወቅ፣ በምእመናን መመረጥ፣ ነውር የሌለባቸው፣ ትዕግስተኞችና የማይሰክሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል። (ፍት.ነገ 1.5)
• ለካህናት፡- 30 ዓመት ሳይሞላቸው ክህነትን አለመቀበል፣ አንድ ሚስት ብቻ ማግባት፣ አብዝቶ አለመጠጣትና አለመሰከር፣ የኃላፊነታቸውን ጥቅም አለመሻትና ለመማታት አለመፍጠን ተጠቃሽ ናቸው። (ፍት.ነገ 1.6 እና 1ኛ ጢሞ 3:1)
• ለዲያቆናት፡- ጭምትነትን ገንዘብ ማድረግ፣ ነውርና ነቀፋ የሌለባቸው መሆን፣ እውነተኛ መሆን፣ ታዛዥነታቸው የተመሰከረላቸው መሆን፣ የማያዳሉና የማይሰክሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
• ለምእመናን፡- መጠመቅ፣ ሥጋ ወደሙ መቀበል፣ ንስሐ መግባት፣ መጾም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ መመጽወት፣ ዐሥራት በኩራት ማውጣትና ልጆችን በሥርዓት ማሳደግ ተጠቃሽ ናቸው። (ፍት.ነገ 1.11)
2. ለምእመናን አንድነት የተሠራ ሥርዓት
ቤተክርስቲያን ምእመናን በኅብረት እንዲኖሩ ሥርዓቶችን ትሠራለች። ለምሳሌ፡-
• ካህናት ሲቀድሱ ምእመናን በኅብረት ጸሎት ያደርሳሉ።
• በጋራ ሆነው ይጸልያሉ።
• በዓላትን በአንድነት ያከብራሉ።
• በሰንበት ጽዋ ማኅበር በአንድነት ይጠጣሉ።
• የቅዱሳንን መታሰቢያ በጋራ ያደርጋሉ።
3. የምእመናን መብትና ግዴታ
• ግዴታዎች፡- መብዓ፣ አሥራት በኩራትና የሰበካ ጉባኤ መዋጮን በወቅቱ መክፈል እንዲሁም መጻሕፍትንና አልባሳትን መለገስ ተጠቃሽ ናቸው።
• መብቶች፡- ትምህርተ ወንጌልን ማግኘት፣ ልጅ ሲወለድ ክርስትና ማስነሳት፣ ጸሎተ ሜሮን መቀባት፣ ቁርባን መውሰድ፣ በኃጢአት ሲወድቁ ከካህን ንስሐ መግባት፣ ሲታመሙ ጸሎተ ቀንዲል መቀባት፣ ጋብቻ ሲፈጽሙ ሥርዓተ ተክሊል ማድረግና ሲሞቱ ጸሎተ ፍትሐት ማግኘት ይገኙበታል።
እነዚህን ሥርዓቶች ጠብቀን በክርስትና ሕይወታችን እንድንጸና እግዚአብሔር ይርዳን!
ይህን መልዕክት ለሌሎችም በማጋራት ያወቅንውን እንድናሳውቅና ና በረከትን እንድናገኝ እንጋብዛችኋለን እንዲሁም ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካላችሁ ግሩፑ ላይ አሳውቁን እንመልሳለን