እስራኤል በሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ፈፀመች‼️
እስራኤል በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኙት የሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተሰምቷል፡፡
የአየር ጥቃቱ የሀውቲ አማፂያን መሪ የሆኑት አቡድል ማሊክ አል ሀውቲ በቴሌቪዥን ንግግር እያደረጉ ባለበት ወቅት መፈፀሙ ሲነገር ፥ በሰነዓ አየር ማረፊያ እና በሄዚያዝ የአሌክትሪክ ሀይልማመንጫ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከሰነዓ በተጨማሪ እስራኤል በአራተኛዋ የየመን ትልቅ ከተማ ሁዴይዳህ የአማፂያኑን ወታደራዊ ይዞታዎች ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሟ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት እስራኤል በየመን መዲና የፈፀመችውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በመዲናዋ በርካታ የእሳት ቃጠሎዎች ተስተውለዋል፡፡
የእስራኤል መገናኛ ብዘሃን እንደዘገቡትም ÷ የአየር ጥቃቱ አማፂያኑ በእስራኤል ግዛት እና በእስራኤል የመርከብ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት የተፈፀመ ነው፡፡
በኢራን እንደሚደገፉ የሚነግርላቸው የሀውቲ አማፂያን ከቀናት በፊት በእስራኤል ቴል አቪቭ የመኖሪያ ሰፈር ላይ በፈፀሙት ጥቃት 16 እስራኤላውያን ተጎድለዋል፡፡
በሰሜናዊ የመን የሚገኘው አማፂ ቡድኑ ለፍልስጤማውያን ድጋፍ ሲል በሚገልፀው ወታደራዊ ጥቃት በቀይ ባህር መርከቦች ላይ ጥቃት ሲፈፅም የቆየ ሲሆን ፥ አሁን ላይ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በመጠቀም እስራኤል ላይ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል፡፡
በአማፂ ቡድኑ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ቀደም ሲል አሜሪካ እና እንግሊዝ የተቀናጀ የአየር ጥቃት መፈፀማቸውን የዘገበው ዥንዋ ነው፡፡
@Esat_tv1