በአማራ ክልል ወራት ያስቆጠረውን መንግሥት እያካሄደ ያለውን 'የዘፈቀደ የጅምላ እስር ዘመቻ' ለማስቆም ዓለም አቀፍ ጫና እንዲደረግ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ‼️
ድርጅቱ መንግሥት እያካሄደው ያለው የዘፈቀደ የጅምላ እስር አራት ወራትን እንዳስቆጠረ በገለጸበት በጥር 20/ 2017 ዓ.ም. መግለጫው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በእስር ላይ እንዳሉ አስታውሷል።
"በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በዘፈቀደ በጅምላ ታስረው ዓለም አቀፉ ዝምታን መምረጡ ከማሳፈር በላይ ነው።
የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች እንዲሁም የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በዘፈቀደ የታሰሩ ዜጎች በሙሉ እንዲፈቱ ያላቸውን ተጽዕኖ በመጠቀም በይፋ ጥሪ ሊያደርጉ ይገባል" ሲሉ የአምነስቲ የምሥራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ ጥሪ አቅርበዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም "የኢትዮጵያ መንግሥት የሕግ የበላይነትን እየተላለፈ ባለበት በዚህ ወቅት ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ቀውስን በቸልታ ሊመለከተው አይገባም" ብለዋል።
ቻጉታህ አክለውም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ክስ እና ያለ ፍርድ ቤት እውቅና ለወራት ታስረው መቆየታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በዚሁ መግለጫቸው ጠቅሰዋል።
"በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ክስ ሳይመሰረትባቸው እንዲሁም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለወራት አስሮ ማቆየት የፍትህ መጓደል እንዲሁም ግልጽ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው" ሲሉ ዳይሬክተሩ ተችተዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለምንም ሕጋዊ መሠረት መታሰራቸው ብቻ ሳይሆን ባለሥልጣናቱ በአማራ ክልል በዘፈቀደ የሚያደርጉትን እስር መቀጠላቸውንም አመልክተዋል።
@Esat_tv1