ቁርአንን ያቃጠለው ግለሰብ በስዊድን ተገደለ‼️
ቁርአንን ካቃጠለ በኋላ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳ ያደረገው ስዊድን ግለሰብ በጥይት ተመትቶ መሞቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የ38 ዓመቱ ሳልዋን ሞሚካ ረቡዕ ማምሻውን በሶደርትልጄ ስቶክሆልም ውስጥ ባለ አፓርታማ ውስጥ መገደሉ ተዘግቧል።
እ.ኤ.አ. በ2023 ሞሚካ የእስልምና ቅዱስ መጽሐፍን ከስቶክሆልም ማእከላዊ መስጊድ በራፍ ላይ ካቃጠለ በኋላ አለመረጋጋት ተፈጥሯል። የስቶክሆልም ፖሊስ ባወጣው መግለጫ በ40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው በፈፀሙው ጥቃት መገደሉን እና በጥይት ከግድያው ጋር በተያያዘ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።
ሞሚካ በተተኮሰበት ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በቀጥታ ስርጭት ላይ እንደነበር የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በስዊድን የሚኖረው እና የዘር ሀረጉ ከኢራቅ የሚመዘዘው ሞሚካ በ2023 ክረምት ለአራት ጊዜያት በአንድ ጎሳ ላይ ቅስቀሳ በማድረግ በነሀሴ ወር ክስ ቀርቦበታል። የስቶክሆልም አውራጃ ፍርድ ቤት ሀሙስ ሊሰጥ የነበረው ብይን "ከተከሳሾቹ አንዱ መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል" ብሏል። ሞሚካ ተከታታይ ፀረ እስልምና ተቃውሞዎችን በማካሄድ በብዙ ሀገራት ቁጣ ቀስቅሷል።
በባግዳድ በሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ ሁለት ጊዜ አለመረጋጋት የተፈጠረ ሲሆን የስዊድን አምባሳደር በዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ከከተማዋ ተባረዋል። የስዊድን ፖሊስ ሞሚካ ቅዱስ መጽሃፉን ያቃጠለበት የተቃውሞ ሰልፍ በሀገሪቱ በነጻ የመናገር ህግ መሰረት ነው ሲል ተጠያቂ አለማድረጉ ቁጣን አስከትሎ ነበር። መንግስት በኋላ በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ ቅዱስ መፅሃፍን ማቃጠልን የሚያካትቱ ተቃውሞዎችን ለማስወገድ ህጋዊ መንገዶችን ለመፈለግ ቃል ገብቶ ነበር።
@Esat_tv1