የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን በአንድ አጠቃሎ የያዘ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ‼️
በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት የውስጥ አቅም ለምቶ ስራ ላይ የዋለው መተግበሪያው በአንድሮይድ እና አይኦኤስ (iOS) ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ለህዝብ ይፋ ሆኗል።
መተግበሪያው በተለያየ ምክንያት የፋይዳ ቁጥር የጠፋባቸው ወይም ያልደረሳቸው ወዲያውኑ መልሰው ማስላክ የሚችሉበት መሆኑን የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቤኔዘር ፈለቀ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በመተግበሪያው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በዲጂታል መልኩ ለማግኘት እንዲሁም አውርዶ ለመያዝ እንደሚቻልም ነው ኃላፊው የተናገሩት።
መተግበሪያው የተለያዩ ሂደቶችን አልፎ ከመረጃ መረብ ደህንነት አገልግሎት የብቃት ማረጋገጫ አግኝቶ ወደ ስራ መግባቱንም አስረድተዋል።
በምዝገባ ወቅት በባለሙያ ምክንያት የተሳሳተን የስነህዝብ መረጃም ጣቢያ ድረስ መምጣት ሳያስፈልግ በስልክ ማረም እንዲሁም የአድራሻ እና የኢሜል ለውጥ ሲኖር ካሉበት ሆኖ ማደስ የሚቻልበት ነው።
መተግበሪያው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በካርድ መልክ አሳትሞ ለመያዝ፣ የካርድ ህትመት ለማዘዝ፣ አስተያየት እና ቅሬታ ለማቅረብ እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችል ለአጠቃቀም ቀላል እና ምቹ መሆኑንም አቶ አቤኔዘር ገልፀዋል።
ይህን መተግበሪያ ጨምሮ የተለያዩ የደንበኞች ፖርታሎች በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ባለሙያዎች መልማታቸውንም የፅህፈት ቤቱ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቤኔዘር ፈለቀ ተናግረዋል።
@Esat_tv1