ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ‼️
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ የተቀናጀ የሴቶች እና ልጃገረዶች ጤና ምላሽ ፕሮጀክትን ለማስተዋወቅ እና ለመተግበር የሚውል የ60 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ፕሮጀክቱ በአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለተለያዩ ጉዳቶች የተጋለጡ ሰዎችን የሚደግፍ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት በአገር አቀፍ ደረጃ የጤና ዘርፉን በማጠናከር 15 ሚሊዮን ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዲቪዥን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ተፈራርመዋል።
@Esat_tv1