ፕሬዚዳንት ትራምፕ እንግሊዝኛን የሥራ ቋንቋ የሚያደርግ ትዕዛዝ ሊፈርሙ ነው‼️
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንግሊዝኛን የአሜሪካ የሥራ ቋንቋ የሚያደርገውን ትዕዛዝ ሊፈርሙ ነው።
ምንም እንኳን አብዛኞቹ የአሜሪካ ግዛቶች እንግሊዝኛን እንደ መንግሥታዊ የሥራ ቋንቋቸው አድርገው ቢወስዱትም፤ በሀገሪቱ የ250 ዓመታት ታሪክ ውስጥ እንግሊዝኛን በይፋ የሥራ ቋንቋ ለማድረግ ሲታሰብ የመጀመሪያው እንደሆነ ታውቋል።
እንግሊዝኛ በይፋ እንደ የሥራ ቋንቋ የተወሰነ ባይሆንም፤ ከተለያዩ ሀገራት ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ሰዎች ማሟላት ከሚገባው መስፈርቶች አንዱ እንግሊዝኛ ቋንቋን መቻል እንደሆነ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን አገልግሎት መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከሦስት አራተኛ በላይ የሚሆኑት አሜሪካውያን እንግሊዝኛን የሚጠቀሙ ቢሆንም፤ ሌሎች ከ350 በላይ በላይ ቋንቋዎች በሀገሪቱ እንደሚነገሩ ኤን.ቢ.ሲ የአሜሪካ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል።
@Esat_tv1