🌍ምክር ለወዳጅ
📍ወዳጄ ሆይ
ድንቅ ሕይወት ለመኖርና ሕልምህን ለማሳካት ፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም ። ሕልሙ ያንተ ነው ፤ የታየህም ለአንተ ነው ። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብህ አንተ ራስህ ነህ ። አንተ ለሕልምህ ምንም ዐይነት ዋጋ ሳትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች ለአንተ ሕልም ዋጋ እንዲከፍሉ መጠበቅ የለብህም ። አንተ ለሕልምህ የመጨረሻውን ዋጋ እና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ስትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች መረዳት ይጀምራሉ ። ራስህን ስትቀይር ፣ ሌሎች ሰዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ ። ራስህን ስትቀይር ፣ ሁሉም ነገር መቀየር ይጀምራል ። ሕይወትህ ፣ ቤተሰብህ ፣ ሥራህ ፣ ገቢህ ፣ ጤንነትህ እንዲሁም የምትፈልገው ነገር ሁሉ እንዲቀየር ፣ በመጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ ። ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው ።
📍ወዳጄ ሆይ
ጓደኛ፣ወዳጅ፣ዘመዴ ያልከው ባስቀመጥከው ቦታ ባታገኘው እንደ ነብር በድንገት ተቆጥተህ እላፊ ነገር ውስጥ ዘለህ አትግባ!... ትርፍ ንግግር ሁሌም ቢሆን ሕሊናን ከማቆሸሽ ያለፈ ውጤት ከቶም የለውም፡፡ ይልቅስ ነገሮች ሁሉ ለበጎ ናቸው የሚባለውን የአባቶች ብሂል አስታውስና ነገሩን ናቅ አድርገህ እለፈው። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም።
📍ወዳጄ ሆይ
ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤ አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣ በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
📍ወዳጄ ሆይ
አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም። መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።
📍ወዳጄ ሆይ
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል " የሚለውን ስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።
📍ወዳጄ ሆይ
እልህ ከራስ ጋር ገመድ መጓተት ነው ። የማይቀጥሉ ነገሮችን መሬት ላይ አስቀምጣቸው ፤ አየር ላይ ከተበተኑ ጉዳት ያመጣሉ ። “የጨዋ ልጅ ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል” እንዲሉ ። የሃያ ዓመቱም የሰማንያ ዓመቱም ሁለቱም የዕድሜ ስስት አለባቸው ። በምናልባት መኖር ጉልበት ይጨርሳል ። ውሳኔ ማጣትም ዕድሜን ይፈጃል ። መኖርህ አለመኖር እንዳይሆን ተጠንቅ ። እንዳትዋረድ ክፉ ጠባይህን አርቅ እንጂ እንዳያዋርዱኝ ብለህ ግን እግርህን አታሳቅቅ።
📍ወዳጄ ሆይ
ያለ መጠን ማድረግ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን
ውጥረትን ያስከትላል አፍ የሚችለውን እጅ ይመጥነዋል እንዲሉ ለሁሉ ነገር መጠን፣ልክ፣ገደብ አለው፡፡ በርሜል ውስጥ የተጠራቀመ ውሃ ከሞላ መፍሰሱ አይቀርም፡፡ መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ።
💎እናም ወዳጄ
ጎደለብኝ በምንለው ጎን ብቻ ነገሮችን ካየን ህይወት መቼም አትሞላም ! ያለንን የሞላውን ግን በደንብ ስንመለከተው ህይወት በራሷ እርካታን ትሰጠናለች ! ያለን የለንም ከምንለው ሁሉ ይበልጣል፣ የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ። ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot