🛑ሠላም ከውስጣችን የሚመነጭ፣ ከቅን አስተሳሰባችን ተምጦ የሚወለድ፣ ከደግ ልቦናችን የሚፈለቀቅ ውስጣዊ ሐብት ነው፡፡ ሠዎች ሠላምን ፍለጋ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ አንዳንዶች ‹‹ሠላምን ማግኘት የምንችለው በጦርነት ነው›› በሚል ፈሊጥ ጠብመንጃ ያነሳሉ፡፡ ጥቂቶች ‹‹ካልደፈረሠ አይጠራም›› በሚል ሃሳብ አደፍርሠው ማጥራትን ይሻሉ፡፡ ነገር ግን ልፋታቸው ከንቱ ሲሆን እናያለን፡፡ በአሸናፊነትና ድል በመንሳት የሚገኝ ሠላም ዕረፍት የሚሠጠው ለጊዜው እንጂ ቋሚ ሠላም አያስገኝም፡፡ ተሸናፊዎቹ ጊዜ ጠብቀውና ዕድል ሲቀናቸው ሠላሙን ሊያደፈርሱት ይችላሉና፡፡
🔷ሠዎች ሠላምን መፈለግ ያለባቸው መጀመሪያ ከራሳቸው ነው፡፡ ጥቂቶች ሠላማዊ ሕሊናን መፍጠር አቅቷቸው ሠላምን ፍለጋ ሲዋትቱ እናያለን፡፡ ለራሳቸው እንኳን ቅድሚያ ሠላም አልሠጡትም፡፡ አዕምሯቸውን በሠላማዊ ሃሳብ አልሞሉትም፡፡ ልቦናቸውን ለሠላም አላስገዙትም፡፡ ስሜታቸውን በሠላማዊ አመለካከት አልገሩትም፡፡ ጥቂቶች እንደውም የሌሎችን ሠላም በመንሳትና ሠላማቸውን በማደፍረስ ሠላም የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡
♦️ሠላም ከራስ፣ ከቤተሠብ፣ ከመንደር፣ ብሎም ሐገር ጋር ሊደርስ የሚችል እንጂ ከውጪ በጉልበት ወይም በገንዘብ ገዝተን የምናመጣው አይደለም፡፡ ሠላምን መፍጠር የሚችለው ራሱ ሠው ነውና፡፡ በግለሠብ ያለው ሠላም ተሰብስቦ የቤተሠብ፣ የመንደር ብሎም የሐገር ሠላም ይሆናል፡፡
አልበርት አንስታይን ስለሠላም ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
‹‹ሠላምን በሃይል ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላም ዕውን ሊሆን የሚችለው በጋራ መግባባት ብቻ ነው፡፡›› ይለናል፡፡
📍እውነት ነው! ሠላምን ማስፈን የሚቻለው በመግባባት፣ ሃሳብን በሃሳብ በማዋሃድ፣ የጋራን ጥቅም በእኩልነት በማስጠበቅ፣ ‹‹እኔ ብቻ ይድላኝ›› የሚሉትን ስግብግብ አስተሳሰብ ወደጎን በማለትና በማስወገድ ጭምር ነው፡፡ መግባባት ሲባል ሠጥቶ መቀበል፤ ተቀብሎ መስጠት ያለበት መርህ ነው፡፡ ለሌላው ሠላም ሳንፈጥር ለራሳችን ሠላም ማግኘት አንችልም!
💎ወዳጆች የሐገርም ሠላም ዕውን የሚሆነው እያንዳንዳችን በምናዋጣት የሠላም አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ ሠላማዊ ሠው ሌሎችን ያከብራል፣ ሠላማዊ ሠው የሌሎችን መብትና ነፃነት ያስጠብቃል፣ ሠላማዊ ሠው እሱ የሚያስፈልገው ሁሉ ሌሎችም እንደሚያስፈልጋቸው ቀድሞ ስለሚያውቅ ጥቅማቸውንና ሕይወታቸውን አይቀማም፡፡ ግና ግን ሠላምን በፖለቲካ አሻጥር፣ ጠልፎ በመጣል ሴራ እውን ማድረግ ፈፅሞ አይቻልም፡፡ ሌሎችን በመጣል የሚገኝ ሠላም እውነተኛ ሠላም አይባልም፡፡
ለዚህም እኮ ነው ዳላይ ላማ፡-
‹‹እያንዳንዱ ግለሠብ ሠላሙን በመፈለግ ሂደት ውስጥ የዓለም ሠላምን ይወስናል!›› የሚለን፡፡
ሠላም ምንጩ ግለሠብ ነው፤ መድረሻው ሐገር ነው፤ ወሠኑ ደግሞ ዓለም ነው፡፡ ሠላምን በመፈክር፣ በዘፈን፣ በግጥም፣ በቀረርቶ፣ ወዘተ ነገሮች ማስፈን አንችልም፡፡
💡እነዚህ ያለን ወይም የነበረን ሠላም ለማጎልበት ይጠቅሙ ይሆናል እንጂ የሠላም ምንጭ መሆን ግን አይችሉም፡፡ የሠላም ምንጩ ግለሠብ ነው፡፡ ያ ግለሠብ ደግሞ ለሠላም ካለው አመለካከት ጋር በተያያዘ የራሱንም ሆነ የአካባቢውን፣ አልፎ ተርፎም የሐገሩን ሠላም ይወስናል፡፡ በአንድ ሠላም በሌለው ግለሠብ ምክንያት ቤተሠብ፣ አካባቢ፣ ሐገር እንዴት እንደሚሸበር በዓለማችን እያየን ነው፡፡
🔑የሠላም መነሻው ግለሠብ ነውና እያንዳንዱ ሠው ሠላሙን ይፍጠር፣ ሠላሙን ያስጠብቅ፣ የሌሎችንም ሠላም ያረጋግጥ፡፡ በተለይ መጪው ትውልድ ሠላማዊ እንዲሆን ለልጆቻችን ሠላምን በተግባር እየከወንን ሠላምን እናስተምራቸው፤ እርስ በርስ በሠላም በመግባባትና በመተራረቅ የሠላም አብነት ሆነን እናሳያቸው፡፡
ሠላም ለዓለማችን! ሠላም ለሃገራችን!ዘመኑ ሠላማችንን የምናረጋግጥበት ይሁን።
ውብ ጊዜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot