▪️|| ትንፋሽ የሚሰጠዉ አርሰናል !
- አንድ ወቅት ዕዉቁ ተንታኝ አላዛር አስገዶም ምን አለ ፤ አርሰናል ብዙ ጨዋታዎች ላይ በመጀመሪያ 1 እና 2 ደቂቃዎች ላይ ግብ ያስቆጥራል ። ነገር ግኝ ወዲያዉ ነዳጁን ረግጦ ደጋግሞ ከማስቆጠር ይልቅ ፍሬን ይዞ መጀመሪያ ባገባዉ ጎል አቻ ላለመሆን ሲጨነቅ ይታያል አለ ። ምንም እንኳን ላወራ የመጣሁት ስለ ዋንጫ ፉክክር ድክመት ቢሆንም አሌ ከሰጠዉ ምሳሌ ጋር ይመሳሰላል ። ሊቨርፑል በዚህ አመት ነጥብ ሲጥል አይተናል ነገር ግን አርሰናል ያንን ዕድል ተጠቅሞ ትንፋሽ ከማሳጣት ይልቅ አብሮት ነጥብ ጥሎ ትንፋሽ ሲሰጠዉ ብዙ ጊዜ አይተናል ። ከአንድ አጋጣሚ ዉጪ አርሰናል ሊቨርፑል ሲጥል አብሮ ጥሏል ።
- በእኔ ዕይታ የ አርሰናል ዕድል አለመጠቀም እንጂ ነጥቡ የዚህን ያህል አይሆንም ፤ መሪም ሊቨርፑል መሆኑ ያጠራጥረኛል ። ይሄ ችግር ከ ስነ ልቦና ይሁን አላዉቅም ግን ዕድሎቹን አይጠቀምም ። እኔ በግሌ ሲቲ የበላባቸዉ ሁለት አመት ላይ ተበልጠን ነዉ ብዬ አላምንም ፤ አሳልፈን መጠቀም ሳንችል ሰጥተን ነዉ ። ሊቨርፑል ዘንድሮ በጣም ምርጥ ብቃት ላይ እያለ እንኳን እንደሚጥል እንናዉቅ ነበር ግን አርሰናል ዕድሉ እንደሚጠቀም ግን እርግጠኛ አልነበርንም ። ሲቲ ቢሆን መሪዉ ድሮ ነበር ያመነዉ ፤ ሊቨርፑል ግን ዕድል ይሰጣል ። ምርጡ ሲቲ በ 2 ነጥብ ከሚመራን ሊቨርፑል በ 8-9 ነጥብ ቢመራን እመርጣለሁ ።
• ሁለተኛ ካለዉ ይልቅ አንድኛ ያለዉ ሁሌ ጫና አለበት ! ይሄ የሚሆነዉ ግን ተከታዩ የራሱን ስራ ሰርቶ ትንፋሽ ካሳጣ እና አንገቱ ስር ከተነፈሰ ብቻ ነዉ !
"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL