በመቐለ ዩንቨርስቲ ከምግብ ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች መኖራቸው ተገለጸ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሆነው ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ፤ በመቐለ ዩንቨርስቲ የአሪድ ግቢ እና ዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመ የመብት ጥሰትን በተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የቀን የምግብ በጀትን ከ22 ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ካደረገ በኃላ አዲስ የምግብ ዝርዝር ይወጣል ተብሎ ለተማሪዎች የተነገረ ሲሆን፤ በታሕሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲሱ የምግብ ዝርዝር መሰረት በፊት ሁለት ዳቦ የነበረው የተማሪዎች የጥዋት ቁርስ ወደ አንድ ዳቦ ተቀንሶ መቅረቡን ተከትሎ በግቢዎቹ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተገልጿል።
ተማሪዎች ከተማሪ ተወካዮች ጋር የሚያገናኝ እና ቅሬታቸው የሚገልፁበት 'የተማሪዎች የቴሌግራም ገጽ' ያላቸው ሲሆን፤ ከምግብ ጋር ተያይዞ ያላቸውን ተቃውሞ በተደጋጋሚ ያነሱ ተማሪዎች በገጹ አስተዳዳሪዎቸ ከገጹ መሰረዛቸው ተነስቷል።
በዚህም ከተመራጭ ተማሪ ተወካዮች ቁጥጥር ውጪ የሆነ የራሳቸው 'አማራጭ የቴሌግራም ገጽ' በመክፈት መወያየት ሲጀምሩ፤ አማራጭ ገጹን ከፈቱ የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ታሕሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ ፀጥታ አካላት ታስረዋል ተብሏል።
"የተማሪ ተወካዮች የምግብ ብልሽት ከሚፈጥሩ የዩንቨርስቲው አመራር እና የምግብ ግብዓቶች አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ጋር ግንኙነት አላቸው" የሚል ጥርጣሬ መኖሩም ተጠቁሟል።
ይህን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞና ረብሻ፤ 14 ተማሪዎች መታሰራቸውን የተነገረ ሲሆን፤ የታሰሩበት ቦታም ዓዲ ሓቂ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን አሐዱ ከሪፖርቱ ለመረዳት ችሏል፡፡
የታሰሩት ተማሪዎች ቤተሰብ ሆነ ሌላ ጠያቂ እንደማያገኛቸው እንዲሁም፤ ከታሰሩት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ስላሉ ሕክምና ማግኘታቸውና አለማግኘታቸው አለመታወቁንም ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ አንስቷል።
ከታሰሩት ተማሪዎች የተለቀቁ ተማሪዎች አሉ የተባለ ሲሆን፤ "ገና ያልተለቀቁ ተማሪዎች ፍ/ቤት መቅረባቸውና አለመቅረባቸው አይታወቅም" ብሏል።
በዚህም "በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 16 መሰረት የተደነገገውን 'ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እና ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ድብደባ፣ አያያዝ ወይም ቅጣት መጠበቅ አለበት' የሚሉ ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃዎች ተጥሰዋል" ሲል ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ ከሷል፡፡
የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ይህንን መሰረታዊ በሕገ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች የተደነገጉ መብቶች በመጣስ ከፍተኛ ድብደባ እና ማሰቃየት ያደረሱ የፀጥታ አካላት፣ ትዕዛዝ የሰጡ እና ወደ ግቢው እንዲገቡ የፈቀዱ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ምርመራ እንዲያስጀምርም ተጠይቋል።
(አሐዱ ሬዲዮ)
⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news
https://t.me/Ethio_Education_24