በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ለዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከታህሳስ 6 እስከ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም መከናወኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ከ608 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፤ ክልሎች በኦንላይን እና በወረቀት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ እስከ የካቲት 25/2017 ዓ.ም ድረስ ለይተው እንዲያሳውቁ ይጠበቃል፡፡
የፈተና ዝግጅቱ ከኢኮኖሚክስ በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት አይነቶችን ያካተተ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ኢኮኖሚክስ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የገባ በመሆኑ ለዚህ ዓመት ከ12ኛ ክፍል ብቻ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተዋል። #ENA
⚡️ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች👇 & ለ Remedial
https://t.me/Ethio_Education_24_news
https://t.me/Ethio_Education_24