🚨ማሳሰቢያ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ባሉበት
ጉዳዩ፦ በአካዳሚክ ምክንያት ለተባረረ (dismissed) ተማሪ የኮርስ ኤግዘምሽን በተመለከተ ስለማሳሰብ ይሆናል፤
የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም እና የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለማቋቋም በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ያስችለው ዘንድ በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያለሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡
ስለሆነም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀን 23/01/217 ዓ.ም በቁጥር 8/256/81/17 በተፃፈልን ደብዳቤ አንድ ተማሪ በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም በሚባረርበት ጊዜ ተማሪው ብቁ አለመሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ በአዲስ መልክ ሌላ ተቋም ውስጥ (በትምህርት ዘመኑ በተቀመጠው የመቁረጫ ነጥብ ውጤት የሚያስገባው ከሆነ) ተመዝግቦ ቢማር ቀድሞ በተባረረበት ተቋም በአንዳንድ ኮርስ ያገኘው ውጤት ኤግዘምት የማይደረግ በመሆኑ ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
@Ethiopiafastnews