ለፕሪሚየር ሊጉ ዳኞች ሲሰጥ የነበረው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ለ24 የፕሪሚየር ሊጉ ዳኞች የተሰጠው የአምስት ቀናት የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በተመረጡ ርዕሶች ላይ ጥር 29/2017 የተጀመረው መርሃ ግብር በክፍል ውስጥ የንድፈ ሃሳብ እና የቪድዬ ትንተና እንዲሁም እና በሜዳ ላይ የፊትነስ የተግባር ልምምድ ተካቶ ተሰጥቷል።
ስልጠናውን አንስትራክተር ግዛቴ አለሙ፣ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ም/ፕሬዝዳንት ኢ/ር ሊድያ ታፈሰ እና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባል እና የአካል ብቃት አሰልጣኝ ኢ/ር ክንዴ ሙሴ ሰጥተዋል። የካቲት 02/2017 በሰላም አዳማ ሆቴል የመዝጊያ ፕሮግራም ሰልጣኝ ዳኞች መርሃ ግብሩን ላዘጋጀው አካል እና አሰልጣኞቻቸው ምስጋና አቅርበዋል።