በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ451 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ
********
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም )
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በግምገማው የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች ፣ የሁለቱም ተቋማት ዳይሬክተሮች ፣ የጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የቅ/ ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሐገር ውስጥ ታክስ 254.9 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 247.7 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 97.2 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመዋል።
በጉምሩክ በኩል ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 190.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 203.8 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 106.7 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
በድምሩ ከሃገር ውስጥ ታክስ እና ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ 445.8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 451.4 ቢሊዮን ብር ወይም የዕቅዱን 101 በመቶ መሰብሰብ እንደተቻለ ጠቁመዋል።
የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ106 . 7 ቢሊዮን ብር ወይም በ110 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
ሚኒስትሯ አክለውም ፤ በመንግስት የተወሰደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ እና ጠንካራ የክትትል ስርዓት መዘርጋቱና መተግበሩ ለገቢ አሰባሰቡ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጉዳዮች መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ከገቢ አሰባሰቡ ባሻገር በህግ ማስከበር ስራዎች ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውን ወ/ሮ ዓይናለም አስገንዝበዋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራትም ከ8.9 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የወጭና የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረውን 107.24 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ አብራርተዋል።
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission