ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት የተሳካ አፈጻጸም መንግሥት ለሰላምና ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው›› ሃና አርዓያ ሥላሴ፣ የፍትሕ ሚኒስትር

‹‹መሬት ላይ ምንም የተፈጸመ ነገር የለም››
የትግራይ ክልል
‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት የተሳካ አፈጻጸም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም፣ ለሰብዓዊ መብቶችና ለኢትዮጵያውያን መበልፀግ ያለውን ያልተገደበ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው፤›› ሲሉ የፍትሕ ሚኒስትሯ ሃና አርዓያ ሥላሴ ገለጹ፡፡
የፍትሕ ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው፣ እ.ኤ.አ. እስከ መጪው ሚያዝያ 4 ቀን 2025 በሚቀጥለው የሰብዓዊ መብት አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ነው፡፡
ሚኒስትሯ በንግግሯቸው በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት ታጣቂዎች መካከል የተካሄደውን ጦርነት እንዲቆም ያደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት፣ ‹‹ስኬታማ አፈጻጸሙ የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድና ከዚያም ያለፉ ችግሮችን በሰላም ለመፍታት ላለው ቁርጠኛነት ምስክር ነው፤›› ብለዋል፡፡
 እ.ኤ.አ. ከ2025 እ.ኤ.አ. እስከ 2027 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139062/


የመንግሥትን ትኩረት በእጅጉ የሚሻው የኢትዮጵያ ቴኒስ

መጠሪያው ‹‹ጀ30›› የተሰኘው ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ዓለም አቀፍ የቴኒስ ሻምፒዮና፣ ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ቴኒስ ክለብ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በክለቡ ፕሮጀክት ያደገው ዳዊት ሸለመው ኢትዮጵያን በመወከል በሻምፒዮናው ድንቅ ብቃት ካሳዩ ተወዳዳሪዎች አንደኛው ሆኗል፡፡  ዳዊት ከግሪካዊው ጋር በጥንድ ባደረገው የፍፃሜ ጨዋታው የብር ሜዳሊያን አግኝቷል፡፡ 
ከ25 አገሮች በሁለቱም ፆታ በርካታ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የቴኒስ ሻምፒዮና፣ በኢትዮጵያ ሲካሄድ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ዘርፉ ከማዘውተሪያ ጀምሮ የመንግሥትን ትኩረት በእጅጉ የሚሻ ስለመሆኑ ጭምር የስፖርቱ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ እንደ አገር፣ በዓለም አቀፍና በአኅጉር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃም ይህ ነው የሚባል ተሳትፎና እንቅስቃሴ እያደረገች አለመሆኑን የሚናገሩት እነዚሁ ባለሙያዎች፣ ለዚህ በዋናነት እንደ ምክንያት አድር...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.proworksmedia.com/139007/


የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የፍጆታና የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ሊያደርግ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የፍጆታ የአገልግሎት ታሪፍ ተመን ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ላይ 0.50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ታሪፍ 0.60 ሳንቲም እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣ የአገልግሎት ክፍያ ተመንን በተመለከተ ለድኅረ ክፍያ አሥር ብር ከ95 ሳንቲም ሲከፍሉ፣ ለቅድመ ክፍያ አራት ብር ከ18 ሳንቲም እንደሚከፍሉ ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ ያሳያል፡፡
የመኖሪያ ቤት ታሪፍን በተመለከተ ከ51 እስከ 100 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች አንድ ብር ከ49 ሳንቲም፣ ከ101 እስከ 200 ኪሎ ዋት ሁለት ብር ከ67 ሳንቲም፣ ከ201 እስከ 300 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች ሦስት ብር ከ84 ሳንቲም እንደሚከፍሉና በየኪሎ ዋቱ መጠን ክፍያው የሚለያይ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ተመንም እንደ ኪሎ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139077/


የሆርቲካልቸር ፓርኮች ማቋቋሚያ ስትራቴጂ ይፋ ሊደረግ ነው

በሃይማኖት ደስታ
በኢትዮጵያ የተለያዩ የሆርቲካልቸር ፓርኮች ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲቋቋሙ የሚያደርግ ስትራቴጂ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ተገለጸ፡፡
ረዥም ጊዜ ወስዶ የተከለሰው አገር አቀፍ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ በርካቶች ጥሩ አቅም የሚፈጥር መሆኑን፣ በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብደላ ነጋሽ ለሪፖርተር ተናግረዋል።
አቶ አብደላ እንደተናገሩት፣ ስትራቴጂው በአነስተኛ ይዞታ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ሌሎች አካላትን የበለጠ ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል ነው። ‹‹ይህም ለአገራችን ትልቁ ማነቆ የሆነባት የውጭ ምንዛሪ የማግኘት ችግርን ለመቅረፍ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከዚሁ ጋር ተያይዞ የባህር በር የለንም ብለን የምናስበውን ወደ ልማት ከቀየርንና ከሠራን፣ ያንን ታሪክ የሚቀይር አንዱ ንዑስ ዘርፍ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139059/


ኢዜማ ለቅቡልነት መታገል ያለብኝ አሁን ነው አለ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፓርቲያቸው ለቅቡልነት መታገል ያለበት አሁን መሆኑን ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አርቆ ከሚመለከትና ተሻጋሪ (ስትራቴጂካዊ) ከሆኑ ግቦች ይልቅ በአጭር ግዜ (ታክቲካዊ) ዕይታዎች ላይ መጠመዱን የተናገሩት መሪው ይኼው አርቆ ያለመመልከት ችግር ደግሞ ፓርቲያቸውን በውስጡ ሲንጠው እንደቆየ ገልጸዋል፡፡ ዘለቄታዊና ረዥም ጊዜ የሚቆይ ሐሳብና ስትራቴጂ ይዞ መምጣት የፓርቲው መሠረታዊ ግብ መሆኑን በመጠቆም ይህን በግልጽ ማበጀቱን ጠቅሰው ሁለተኛና ቀጥሎ የሚመጣ ላሉት ለቅቡልነት መታገያው ጊዜ አሁን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ላለፉት 50 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዑደት የተሳሳተና የወደቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካም ሆነ ማኅበረሰቡን በግራ መጋባት ውስጥ መጣሉን አመልክተው ኢዜማ ዘመን ተሻጋሪ ግብ ላይ አተኩሮ መታገል እንደሚኖርበት ጠቁመዋል፡፡  
ከየ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139027/


ከአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች 40 በመቶ የሚሆኑት ዓመታዊ ክፍያቸውን እንደማይከፍሉ ተገለጸ

ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን ዓመታዊ ወጪ ከአኅጉሩ ውጭ ካሉ የአውሮፓና አሜሪካ ምንጮች በሚገኝ ገንዘብ ዓመታዊ ወጪውን የሚሸፍነው የአፍሪካ ኅብረት፣ 40 በመቶ የሚሆኑ አባል አገሮች ዓመታዊ የአባልነት ክፍያቸውን እንደማይከፍሉ ተጠቆመ፡፡
በኅብረቱ ድረ ገጽ ከሰሞኑ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኅብረቱ የሚያወጣቸውን ፕሮግራሞች፣ ዕቅዶችና ተግባራት በአባላት አገሮች የማይደገፉ በመሆናቸው፣ ተገማች፣ ቀጣይነት ባለው መንገድ እንዳደማይመራና ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘቡ ለሌላ ዓላማ መዋሉን ጠንካራ ተጠያቂነት አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የአባል አገሮቹ የኅብረቱን ዓመታዊ በጀት ለማቀድና በዕቅዱ ለመመራት ያላቸው ሚና ዝቅተኛ መሆኑን የገለጸው የኅብረቱ መረጃ፣ የፋይናንስ አመራር መዘርዝርና በተጠያቂነት መርሕ የሚመራበት ሥርዓት አለመኖሩን አስታውቋል፡፡
መረጃው እንደሚያሳየው ሕግና መመርያ፣ ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ዘዴ እንደሌለውና ሀብት በምን ሁኔታና...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139056/


ነጋዴ ሴቶችን ለማስተሳሰር ያለመው የኮሜሳ የንግድ ትርዒትና የቢዝነስ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

 የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) አባል አገሮች ውስጥ የሚገኙ ነጋዴ ሴቶችን ለማስተሳሰር ያለመ የኮሜሳ የንግድ ትርዒትና የቢዝነስ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን 6ኛው የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች የንግድ ትርዒትና የቢዝነስ ኮንፈረንስን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው የኮሜሳ አባል አገሮች ነፃ የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩና ይህም ውጤት እየመጣ ነው ተብሏል፡፡ የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር ወ/ሮ ስምረት ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት ኮሜሳ የተቋቋመበት ዋነኛ ዓላማ በንግድ አማካይነት በአባል አገሮች መካከል ቀጣናዊ ትስስር መፍጠር በመሆኑ በዚሁ አግባብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ይህንን ትስስር ለመፍጠርም በኮሜሳ የተዘጋጁ የተለያዩ ስምምነቶች ያሉ በመሆኑ በዚሁ አግባብ አባል አገሮች ይህንን ስምምነት እየተቀበሉ የሚተገብራቸው ናቸው፡፡ ይህ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139026/


የመሬት መንቀጥቀጥ ከጂቡቲ እስከ አዲስ አበባ በተዘረጋው መንገድ ላይ አደጋ መደቀኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የገቢና የወጪ ንግድ የሚተላለፍበት ከጂቡቲ እስከ አዲስ አበባ የተዘረጋው መንገድ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ መተሃራ አካባቢ ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችልና አደጋ መደቀኑ ተነገረ፡፡
በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ተመራማሪ አቶ ናትናኤል አገኘሁ እንደተናገሩት፣ ፈንታሌ ተራራ ላይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ የማግማ ወይም ቅልጥ አለት ወደ ላይኛው የመሬት ክፍል እየተጠጋ መሆኑን ኢንሳር (INSAR) በተሰኘ የራዳር ቴክኖሎጂ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ይህ በመሆኑም የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ ከተከሰተ ከጂቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ብለዋል፡፡
ማግማው ወይም ቅልጥ አለቱ ፈንድቶ በመንገዱ ላይም ሆነ በሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት፣ ሦስት ተለዋጭ መንገዶች እንዲገነቡ ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡
እ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139072/


#ማስታወቂያ

Tajaajila Liqii Maayikiroo Faayinaansii (ABIL) ilaalchisee odeeffannoo dabalataa argachuuf, marsariitii Baankii keenyaa https://siinqeebank.com/microfinance/#tab-6bb700f6cc2e90a6b30 daawwadhaa.

ስለአቢል፣ የሲንቄ ባንክ ማይክሮፋይናንስ የብድር አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ድረ-ገጽ
https://siinqeebank.com/microfinance/#tab-6bb700f6cc2e90a6b30 ይጎብኙ፡፡


#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER


የመንግሥት መዋቅር ክፍተት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ የግብርና አሠራር በታሰበው ልክ እንዳይተገበር አድርጓል ተባለ


አሠራሩ የአርሶ አደሮችን ዓመታዊ ገቢ ከፍ ያደርጋል ተብሏል

በሃይማኖት ደስታ
ለአርሶ አደሮች 129 በመቶ የገቢ ዕድገት ያስገኘላቸው ዘመናዊ የግብርና አሠራር  በታሰበው ልክ እንዳይተገበር፣ ከላይ እስከ ታች ያለው የመንግሥት መዋቅር ክፍተት መፍጠሩ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የግብርና ሚኒስቴር ከጃፓን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ጋር በመተባበር የካቲት 26 እና 27 ቀን 2017 ዓ.ም ‹‹የተለያዩ የሼፕ አሠራሮች ንቅናቄ›› በሚል መሪ ቃል፣ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ ባካሄደው 11ኛው ‹‹በአነስተኛ ይዞታ ሆልቲካልቸር አምራች አርሶ አደሮችን ገበያ ተኮር የግብርና ዘዴ በማስተዋወቅ የማብቃት ፕሮጄክት (ኢትዮ ሼፕ) ዓለም አቀፍ ዓውድ ጥናት ላይ ነው።
በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብደላ ነጋሽ፣ አሠራሩ አርሶ አደሮች ከ2,000 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ያገኙ የነበረውን ዓመታዊ ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139080/


#ማስታወቂያ


#ማስታወቂያ

#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
       ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251911010170
     +251951574515
TemerRealEstateSalesConsultant


ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ

አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139049/


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#ማስታወቂያ

ዘካ የተቀማጭ ሂሳብ
=========
ዘካዎትን በሲቢኢ ኑር የዘካ ተቀማጭ ሂሳብ ያስቀምጡ፣
እርስዎ ለመረጧቸው ዘካ ተቀባዮች በቀላሉ እናደርስልዎታለን!

#CBE #cbenoor #zakat #saving
#ዘካ #ቁጠባ #ሂሳብ


#ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ እንኳን ለ1446 ዓ.ሒ የሐጅ ጉዞ በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሐጅ ጉዞ ክፍያዎን በአቅራቢያዎ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በልዩ መስተንግዶ እንዲፈጽሙ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሸሪዓውን መርህ መሰረት ያደረገ ሕብር ሀቅ የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

ሐጀን መብሩር!

ሕብር ሀቅ
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.me/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡


ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com


‹‹የፒያሳ ቆሌዎች›› የጃፓናዊው በረከት

ኢትሱሺ ካዋሴ (ዶ/ር) ጃፓናዊ አንትሮፖሎጂስት የፊልም ባለሙያና ገጣሚ ነው፡፡  ካዋሴ (ዶ/ር) ሕይወቱ ከሙዚቃ ጋር የተሳሰረች የሙዚቃ ምርኮኛ ነው ይሉታል በቅርበት የሚያውቁት፡፡ ታድያ ‹‹ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው›› እንደሚባለው ካዋሴ በሰሜን ኢትዮጵያ ስለሚገኙ አዝማሪዎች ዝና ሰምቶ ጊታሩን በጀርባው አዝሎ  ከሩቅ ምሥራቅ ጃፓን ተነስቶ 10 ሺሕ ገደማ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጦ መዳረሻውን  ኢትዮጵያ ካደረገ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ ካዋሴ (ዶ/ር) ማረፊያውን አዲስ አበባ ያድርጎ ለአንትሮፖሎጂስት ጥናቱ የሚሆነው አካባቢ ሲመርጥ የጎንደር አዝማሪዎች ለግብዓቱ ተመራጭ እንደሆኑ ባገኘው መረጃ መሰረት ሳይውል ሳያድር በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ተጉዞ  ሸዋ፣ ወሎና ጎጃም አቋርጦ መዳረሻውን  ጎንደር ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል አድርጎ እንደነበር ያስታውሳል፡፡

ስለ ጎንደር ውበትና እንግዳ አቀባበል ተናግሮ የማይጠግበው ካዋሴ (ዶ/ር) ‹‹ጎንደሬዎች እን...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138953/


በጄኔቫ እየተካሄደ ባለው የተመድ ጉባዔ 44 አገሮች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ያሳስበናል አሉ


የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ማሳሰቢያውን መሠረተ ቢስ ብለውታል

በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 58ኛው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ፣ 44 አገሮች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ያሳስበናል ሲሉ መግለጫ አወጡ።
ኤ.ኤ.አ. ከየካቲት 24 ቀን 2025 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጉባዔ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ አገሮቹን በመወከል የካቲት 24 ቀን ባቀረቡት መግለጫ፣ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ፣ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግና መደራጀት ላይ ያሉ ገደቦች በመጥቀስ ጋዜጠኞችን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችንና የመብት ተሟጋቾችን ማፈን አሳሳቢ ናቸው ብለዋል፡፡  
በተጨማሪም በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች አሳሳቢነት እየጨመረ መሆኑን የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን መረጃ  ዋቢ በማድረግ እንዲስተካከሉ አሳስበዋል፡፡
የንፁኃን ግድያ፣ ማንገላታት፣ ማሰቃየት፣ በኃይል መሰወር፣ ዜጎችን ከሕግ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138931/


የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ገቢውና ሀብቱ ቢቀንስም ትርፉ አራት ዕጥፍ ማደጉ ታወቀ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጀት ጠቅላላ ገቢ በ12 ቢሊዮን ብር ዝቅ ቢልም፣ ትርፉ በአራት እጥፍ ከፍ ማለቱ ታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ
እስመለዓለም ምሕረት

ድርጅቱ የ2016 ዓ.ም. (June 30, 2024) ኦዲት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የኦዲት ሪፖርቱ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እስመለዓለም ምሕረት የፀደቀው ባለፈው ሳምንት ነው፡፡
በዓመቱ የድርጅቱ የነዳጅ ሽያጭ ገቢ ዓምና ከነበረበት 271 ቢሊዮን ብር ወደ 259 ቢሊዮን ብር ወርዷል፡፡
ይሁን እንጂ ድርጅቱ ቅናሹን በተለያዩ መንገዶች በማካካስ፣ ከፍተኛ የትርፍ ዕድገት ሊያስመዘግብ ችሏል፡፡ አንደኛው መንገድ ወጪን መቀነስ ሲሆን፣ በተለይ ከሽያጭ ጋር የተገናኙ ወጪዎችን በማሻሻልና በመቆጣጠር፣ ወጪውን ከነበረበት 255 ቢሊዮን ብር ወደ 246 ቢሊዮን ብር በማውረድ ወደ ስምንት ቢሊዮን ብር ገደማ ሊያድን ችሏል፡፡
ሌላው ማካካሻ መንገድ በተለይ መንግሥት የነዳጅ ድጎማን በሒ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138908/


ለአንድ ዶላር እስከ 141 ብር ዋጋ የተሰጠበት የሰሞኑ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ

የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ እንዲገበያይ ከተወሰነ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል፡፡ 60 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበት በዚህ ጨረታ 27 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ለአንድ ዶላር የተሰጠው አማካይ የጨረታ ዋጋ 135.6 ብር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡ 
በጨረታው የተሰጠው አማካይ ዋጋ በጨረታው ዕለት ባንኮች ሲያገበያዩበት ከነበረው አማካይ ዋጋ ከአሥር ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑን ያመለክታል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደለገጹት፣ በዕለቱ ተሳታፊ ከሆኑ 27 ባንኮች ውስጥ በዕለቱ የተጫረቱበትን የውጭ ምንዛሪ ያገኙት 12 ባንኮች ናቸው፡፡ እነዚህ አሥራ ሁለት ባንኮች አሸናፊ የሆኑት ለአንድ ዶላር ከ130 እስከ 141 ብር ዋጋ በመስጠት ነው፡፡ በዚህ ጨረታ ላይ አንድ ባንክ ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት 200 ሺሕ ዶላር ማግኘቱን እኚሁ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138992/

Показано 20 последних публикаций.