ኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻ የገዙ ባለድርሻዎች ይፋ አደረገ
-ከአክስዮን ሽያጩ 3.2 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ታውቋል
ኢትዮ ቴሌኮም በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የአስር በመቶ ድርሻ በ121 ቀናት ውስጥ 47,377 ኢትዮጵያዊያን የ10.7 ሚሊዮን አክስዮኖችን መግዛታቸውን ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ለሰዓት በስካይላይት ሆቴል አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ሽያጩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ 712 ሰዎች የ900,000 ብር እና ከዛ በላይ አክስዮን ገዝተዋል። የአክስዮን ሽያጩ እስከ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 121 ቀናት ድረስ 47,377 ኢትዮጵያዊያን 10.7 አክስዮኖችን ገዝተዋል። ከአክስዮን ሽያጩ 3.2 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ታውቋል፡፡
በቀጣይ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለ ስልጣን አሰራር መሰረት ሰዎች በገዙት መጠን የአክስዮን ድልድል ይደረጋል ተብሏል።
የቀሩትን ድርሻዎች ምን መደረግ እንዳለባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑንና መንግሥት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ አማካይነት የሽያጭ ማስታወቂያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም በጥቅምት ወር 100 ሚሊዮን አክስዮኖች ለሽያጭ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።በማስታወቂያው መሰረት አንድ ሰው ዝቅተኛ የመግዛት አቅሙ 33 ሼሮች እንዲሁም ከፍተኛው ደግሞ 3,333 ሼሮችን እንደነበርም ይታወቃል።