‹‹በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ ያስፈልጋል›› - አምነስቲ
በአማራ ክልል ያለውን የዘፈቀ የጅምላ እስር የሚያስቆም አስቸኳይ አለም አቀፍ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ፡፡
በክልሉ መንግስት መር የዘፈቀደ የጅምላ እስር መፈጸም ከተጀመረ ድፍን አራት ወራት ተቆጥረዋል ያሉት የድርጅቱ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ባለበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ ከማሳፈርም በላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የመብት ተሟጋቾች ጭምር በጅምላ ታፍሰው በግፍ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የህግ የበላይነት ተረግጦ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ዓለም በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አይቶ እንዳላየ ማለፉን ሊያቆም ይገባልም ነው ዋና ዳይሬክተሩ ያሉት፡፡
‹‹በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያለምንም የፍርድ ሂደት አስሮ ወራትን ማቆየት በፍትህ ላይ የሚፈጸም አሳፋሪ ስላቅ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ሺዎች ያለምንም የፍርድ ሂደት በእስር መማቀቃቸው ብቻም አይደለም፤ በአማራ ክልል አሁንም የዘፈቀደ እስሩ ቀጥሏል፡፡
በመሆኑም መንግስት በዘፈቀደ እያፈሰ በጅምላ ያሰራቸውን ሊለቅ ካልሆነም ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው የተጠያቂነት የህግ መስፈርቶች ክስ ሊመሰርትና በህግ ሊጠይቃቸው›› እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የሲቪክ ምህዳር እንዲህ ባለ ሁኔታ እየደቀቀ ባለበትና 32 ዓመታትን ያስቆጠረን አንድን ተቋምን ጨምሮ አራት የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ታግደው ስራ ባቆሙበት ሁኔታ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና በአስቸኳይ ያስፈልጋልም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
አምነስቲ ካሳለፍነው ወርሀ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በፌዴራሉ መንግስትና በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እየተያዙ ወደ አራት የጅምላ ማጎሪያዎች መወሰዳቸውን ትናንት ማክሰኞ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በክልሉ የተቀሰቀሰውንና አሁንም የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ በጅምላ ታፍሰው ከታሰሩት መካከል ዳኞችንና አቃቤ ህጎችን እንዲሁም ሌሎች የፍትህ አካላትን ጨምሮ ምሁራን እንደሚገኙበትም ነው የገለጸው።
ጥቅምት ላይ የተለቀቁትን አራት የፍትህ ሰራተኞች ጨምሮ በተያዘው የጥር ወር ሶስት ዳኞችን፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን እና ሥር የሰደደ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር ተለቀዋል ያለው አምነስቲ ሆኖም ግን አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዘፈቀደ ተይዘው እስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑ ባወጣው የሶስት ወራት ሪፖርት በአማራ ክልል ያለው የዘፈቀደ ግድያ፣ እስር፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ተባብሶ እንደቀጠለ በማሳሰብ 72 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ማስታወቁ ይታወሳል።
ኮሚሽኑ፤ ንጹሀኑ ድሮንን ጨምሮ በአየር ጥቃት፣ ዒላማን ባልለየ የጦር መሳሪያ ተኩስ እንዲሁም ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚልና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መገደላቸውን ማስታወቁም የሚታወስ ነው፡፡
በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት 22 ዳኞች እንዲሁም አዋጁ ካበቃ በኋላ 13 ዳኞች በጥቅሉ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ 35 ዳኞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊነትና “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ውን እንደ ሽፋን በመጠቀም ሕገ ወጥ እስራት እንደተፈጸመባቸው ገልጾ የዳኝነት ነጻነት መሸርሸሩ አሳሳቢ እንደሆነ ማስታወቁም አይዘነጋም።