ለአንድ ዶላር እስከ 141 ብር ዋጋ የተሰጠበት የሰሞኑ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ
የውጭ ምንዛሪ በገበያ ዋጋ እንዲገበያይ ከተወሰነ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል፡፡ 60 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበት በዚህ ጨረታ 27 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ለአንድ ዶላር የተሰጠው አማካይ የጨረታ ዋጋ 135.6 ብር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡
በጨረታው የተሰጠው አማካይ ዋጋ በጨረታው ዕለት ባንኮች ሲያገበያዩበት ከነበረው አማካይ ዋጋ ከአሥር ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑን ያመለክታል፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደለገጹት፣ በዕለቱ ተሳታፊ ከሆኑ 27 ባንኮች ውስጥ በዕለቱ የተጫረቱበትን የውጭ ምንዛሪ ያገኙት 12 ባንኮች ናቸው፡፡ እነዚህ አሥራ ሁለት ባንኮች አሸናፊ የሆኑት ለአንድ ዶላር ከ130 እስከ 141 ብር ዋጋ በመስጠት ነው፡፡ በዚህ ጨረታ ላይ አንድ ባንክ ከፍተኛ ዋጋ በመስጠት 200 ሺሕ ዶላር ማግኘቱን እኚሁ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138992/