በጄኔቫ እየተካሄደ ባለው የተመድ ጉባዔ 44 አገሮች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ያሳስበናል አሉ
የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ማሳሰቢያውን መሠረተ ቢስ ብለውታል
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 58ኛው የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ፣ 44 አገሮች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ያሳስበናል ሲሉ መግለጫ አወጡ።
ኤ.ኤ.አ. ከየካቲት 24 ቀን 2025 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጉባዔ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ አገሮቹን በመወከል የካቲት 24 ቀን ባቀረቡት መግለጫ፣ ሐሳብን በነፃነት መግለጽ፣ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረግና መደራጀት ላይ ያሉ ገደቦች በመጥቀስ ጋዜጠኞችን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችንና የመብት ተሟጋቾችን ማፈን አሳሳቢ ናቸው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች አሳሳቢነት እየጨመረ መሆኑን የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንዲስተካከሉ አሳስበዋል፡፡
የንፁኃን ግድያ፣ ማንገላታት፣ ማሰቃየት፣ በኃይል መሰወር፣ ዜጎችን ከሕግ...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138931/