ከአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች 40 በመቶ የሚሆኑት ዓመታዊ ክፍያቸውን እንደማይከፍሉ ተገለጸ
ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን ዓመታዊ ወጪ ከአኅጉሩ ውጭ ካሉ የአውሮፓና አሜሪካ ምንጮች በሚገኝ ገንዘብ ዓመታዊ ወጪውን የሚሸፍነው የአፍሪካ ኅብረት፣ 40 በመቶ የሚሆኑ አባል አገሮች ዓመታዊ የአባልነት ክፍያቸውን እንደማይከፍሉ ተጠቆመ፡፡
በኅብረቱ ድረ ገጽ ከሰሞኑ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ኅብረቱ የሚያወጣቸውን ፕሮግራሞች፣ ዕቅዶችና ተግባራት በአባላት አገሮች የማይደገፉ በመሆናቸው፣ ተገማች፣ ቀጣይነት ባለው መንገድ እንዳደማይመራና ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ገንዘቡ ለሌላ ዓላማ መዋሉን ጠንካራ ተጠያቂነት አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የአባል አገሮቹ የኅብረቱን ዓመታዊ በጀት ለማቀድና በዕቅዱ ለመመራት ያላቸው ሚና ዝቅተኛ መሆኑን የገለጸው የኅብረቱ መረጃ፣ የፋይናንስ አመራር መዘርዝርና በተጠያቂነት መርሕ የሚመራበት ሥርዓት አለመኖሩን አስታውቋል፡፡
መረጃው እንደሚያሳየው ሕግና መመርያ፣ ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ዘዴ እንደሌለውና ሀብት በምን ሁኔታና...
ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/139056/