ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሲሆን
*****************
እንግዲህ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው እንዲህ የሆነው ።" እችላለሁ " መባል የነበረበት " እችላለው " ፣ " እፈልጋለሁ " መባል የነበረበት " እፈልጋለው " ፣ " አመሰግናለሁ " መባል የነበረበት " አመሰግናለው " ተብሎ የተጻፈው ። አሁን አሁን ስህተቱ ተለምዶ ማንሳትም እየቀረ ነው ። ስህተቱ ልክ እየሆነ ነው ። ይህ ግን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ። የቋንቋ ጉዳይን ለማረቅ ስልጣን ያለው ፣ ሌሎች ሲሳሳቱ ማረም ያለበት ተቋም ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አማርኛን የማያውቅ ምሩቅ ለምን በአማርኛ ይጽፋል ? አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም " ሁ " - " ው " ቢባል ምንም ለውጥ እንደሌለው ያስባል ? አይመስለኝም ። እንግዲህ ማን ነው የሚመለከተው ? ሁሉን አቅልለን አቅልለን ቀለልን እኮ ጎበዝ ።
Tewodros Teklearegay