💠ትንሽ አትሁኑ!
፨፨////////፨፨
ሌሎችን ለመተቸት ጊዜ እስክታጡ ድረስ ራሳችሁን በማሻሻል ተጠመዱ፣ ራሳችሁን በማብቃት ቢዚ ሁኑ። ትልቁ ስራ የሰውን ድክመትና ክፍተት ማውጣት ሳይሆን የራስን አውቆና ተረድቶ እርሱን ማሻሻል መሆኑን እንዳትረሱ። ትቺት የዓለምን ህዝብ እኩል የሚያደርግ በጣም ቀላሉ ስራ ነው፣ በምትኩ ራስን ማሻሻል የዓለምን ህዝብ የሚለይ ትልቁና ዋንኛው ስራ ነው። ማንም ልዩነት ፈጣሪ ሰው ልዩነቱን የፈጠረው ለዓመታት ሰውን ተችቶ፣ በሰው ስራ ተሳልቆ ወይም ሰው ላይ አተኩሮ አይደለም። ይልቅ ራሱን አውቆ፣ ማንነቱን ተረድቶ፣ አቅሙን ተገንዝቦ፣ ያለማቋረጥ ራሱ ላይ ሰርቶ፣ በየቀኑ ራሱን እያስተማረና ራሱን እየፈተነ ነው። ራሳችሁ ላይ ማተኮራችሁን ስትቀጥሉ የሰዎችን ድክመትና ክፍተት የመመልከት እድላችሁ እያነሰ ይመጣል። ጊዜያችሁ እጅግ በጣም ውድ ነው። ከቻላችሁ በገንዘባችሁ ግዙት፣ ሌላ ሰው ማድረግ የሚችለው ጉዳይ ካለ እርሱን ለሰው አሸጋግራችሁ ጊዜያችሁን ለተሻለ ነገር ነፃ አድርጉት።
አዎ! ትናንሽ ነገር እያደረጋችሁ ትንሽ አትሁኑ፣ በአሳፋሪ ተግባር ተሳትፋችሁ በራሳችሁ አትፈሩ። ሰዎች ላይ ያለማቋረጥ የነቀፋ ቃላትን መሰንዘር እውቀት ወይም ስልጣኔ አይደለም። ሁሌም ቢሆን ቁጭ ብሎ ማውራት የትናንሽ ሰዎች ባህሪ ነው፣ የሰው ስራን ሁሉ መናቅ የተናቁ ሰዎች ስራ ነው። አትዘናጉ፣ አይናችሁ ውጪ ውጪውን ሲል ማሻሻልና ማስተካከል የሚችለውን የገዛ ማንነቱን ይዘነጋል፣ ራሱን ይረሳል፣ የት ቆሞ ማንን እንደሚተች ማስተዋል ይሳነዋል። ራስን ማወቅን የሚያክል ትልቅ ምድራዊ ጥበብ የለም። ራሱን የሚያውቅ ሰው ከሁሉም በላይ ፈጣሪውን ይፈራል፣ ራሱን ለእርሱ ትዕዛዝና አስተምህሮ ያስገዛል፣ ቃሉን ያከብራል፣ በሰዎች አይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ከመመልከቱ በፊት የራሱ አይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ያስተውላል፣ ግዞቱ ያልሆነው ውጪ ላይ ከማተኮር ግዞቱና ርስቱ በሆነው ራሱ ላይ ያተኩራል። ከአምላክና ከእናንተ በቀር እናንተን የሚያውቅ ሰው የለም። ማንም ስለእናንተ እንዲነግራችሁ አትጠብቁ። ምንም ዙሪያ ጥምጥም መሔድ ወይም ሰውን ማስጨነቅ አያስፈልግም የራስ ግንዛቤያችሁ ምንጭ እናንተ ብቻ ናችሁ።
አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ዝግጁ ካልሆንክ አንዳች ከውጭ መጥቶ የሚቀይርህ ነገር የለም። ዛሬም እንደ ትናንቱ ዋናው የህይወት አጀንዳህ ሰዎች ከሆኑ ከምታስበው በላይ ለውድቀት እየቀረብክ እንደሆነ አስተውል። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የራሳቸውን ውድቀት በሰዎች ለመሸፈን ይሞክራሉ፣ ሰዎችን በናቁና በተቹ ቁጥር ንፁና ከእነርሱ የተሻሉ ሰዎች እንደሆኑ ያስባሉ። ነገር ግን የትኛውም ከሌላው ሊሻል የሚችለው በወሬ ሳይሆን በስራና በስራ ብቻ ነው። ችሎታው ማውራትና መተቸት ቢቻ የሚመስለው ሰው ስራውን ከመስራቱ ውጪ ትቺቱ የሰውን ስሜት እንደሚጎዳና ህልሙን ሊያደናቅፍበት እንደሚችል አያስብም። ብዙ አውቃለሁ፣ ነገሮችን ተረድቼያለሁ፣ ራሴንም አውቃለሁ ካልክ አፍህን ዝጋ፣ ስለሌሎች አይደለም ስለራስህ እንኳን ከልክ በላይ አታውራ። የምር አዋቂ ከሆንክ ስሜትህን ግዛ፣ ራስህ ላይ ሰልጥን፣ ሰዎችን መተቸት አቅቶህ ሳይሆን ጊዜውን እስክታጣ ድረስ በግል ጉዳዮችህ ተጠመድ፣ ትልቁን ጥበብህንም ገልጠህ ለዓለም አሳይ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
💠JOIN and Share👇
💠Group:👇
@Ethio_Entrance_discussion
@Ethio_Entrance_discussion
💠Channel:👇
@Ethiopian_Minister_Of_Education