" ሐኪሞቹ ' መግቧቸው፤ የምግብ እጥረት ነው ' ይላሉ። እኛ ደግሞ ከየት እናመጣዋለን ? ጊዜው ከፋብን " - እናት
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታውቋል።
በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ዓለሙ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የተነሳው ግጭት አንድ ዓመት ከመንፈቅ ያለፈው ሲሆን ከግጭቱ ባለፈ ወረዳው " ዝናብ አጠር እና በተፈጥሮ የተጎዳ ነው " ያሉት ኃላፊው በተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የምግብ እጥረት መከሰቱን አስታውቀዋል።
" ማኅበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን በአግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል " ሲሉ ተፈጥሯዊውን ተጽዕኖ ገልጸዋል።
" ረድኤት ድርጅቶችም ለማኅበረሰቡ አልደረሱለትም " ብለዋል።
በወረዳው ብርኮ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ የካባ የአንድ ዓመት ከሦስት ወር መንታ ወንድና ሴት ልጆቻቸው በምግብ እጥረት " ስቃይ " ውስጥ እንደሆኑ ተናግረዋል።
" ምን አግኝተን እንርዳቸው ? እስካሁን ድረስ በተቻለን ይዘናቸው ነበር። ከአዲስ ዓመት ወዲህ ግን ምንም ነገር የለም። ተያይዞ ቁልጭልጭ ሆነ እኮ? " ሲሉ አስረድተዋል።
" ጡጦ የምልበት ጎን አቅም የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት ወተት አሁን አነሳቸው፤ እንዴት ይድረሳቸው ?. . . የተገኘው ምግብም አልሆናቸው አለ፤ አልስማማቸው አለ "ብለዋል።
ጠላ በመሸጥ ይተዳደሩ ነበሩት ወ/ሮ የካባ ልጆቻቸው ሲታመሙ ስራ እንዳቆሙ ይናገራሉ።
ከቤተሰቦቻቸው ያገኙት የነበረውን የምግብ ድጋፍ በማጣታቸው መቸገራቸውንም ያስረዳሉ።
" ሐኪሞቹ ' መግቧቸው፤ የምግብ እጥረት ነው ' ይላሉ። እኛ ደግሞ ከየት እናመጣዋለን ? ጊዜው ከፋብን። መሬቱ ደረቀ ፤ እናት አባት አንድ ሁለት ኬሻ እህል ይሰጡን ነበር። ከዛ ብሶም ዘመኑ አጠፋው " ሲሉ እርሳቸውም በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው ሕፃናት ልጆቻቸው እየተጎዱ እንደሆነ ገልፀዋል።
አንድ የአካባቢው የጤና ባለሞያ " ጤና ጣቢያ የሚመጡት እናቶች ከሚያጠቡት ልጅ ይልቅ እነርሱ ራሱ የከሱ ናቸው " ብለዋል።
እርሻቸውን በረዶ እንደመታባቸው የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪ አቶ ደሳለው አለባቸውም ፤ ባለቤታቸው እና የ10 ወር መንታ ልጆቻቸው በምግብ እጥረት ተጎድተው ጤና ጣቢያ መግባታቸውን ተናግረዋል።
ባቄላ፣ ገብስ እና ጤፍ ያመርቱ እንደነበር የተናገሩት አቶ ደሳለው፤ " እናት የምትበላው የላትም፤ ልጆቹም የሚጠቡት የለም " ሲሉ ዘንድሮ " የተለየ " ችግር ገጥሞናል ብለዋል።
" በጣም ሲብስብን፤ ሲጨንቀን ወደ ጤና ጣቢያ አመጣናቸው። ሁለተኛ ቀናችን ነው። . . .የምግብ እጥረት ስላለባቸው ተዳክመዋል፤ ከስተዋል" ሲሉ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።
አይና ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ መኮንን አሻግሬ አካባቢው ካለበት ተፈጥሯዊ ችግር በተጨማሪ ከአዲሱ በጀት ዓመት በኋላ የተመጣጠነ የምግብ ላይ የሚሰሩ ረድኤት ድርጅቶች ግብዓት ማቆማቸውን አሳውቀዋል።
አንድ የጤና ባለሞያም ወረዳው የምግብ እጥረት ችግር ያለበት መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ ችግሩ ጎልቶ መታየቱን ተናግረዋል።
በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የአልሚ ምግቦች እና መድኃኒቶች አቅርቦት በመስተጓጎሉ ነፍሰ ጡር እናቶች እና ሕፃናት " ለተወሳሰበ ምግብ እጥረት " እንደተዳረጉ ገልጸዋል።
በታኅሣሥ ወር መጀመሪያ የጤና ባለሞያዎች ለክትባት ዘመቻ ሲወጡ ነፍሰ ጡር እናቶች እና ሕፃናት ' በሥርዓተ ምግብ ልየታ ' " የከፋ " የምግብ እጥረት ላይ እንደሆኑ መታዘብ ችለዋል።
በቡግና ወረዳ ካሉ 16 ቀበሌዎች በተለይም ላይድባ፣ ብርኮ፣ ጉልሃ፣ በርኳኳ እና ፈልፈሊቅ በተባሉ ቀበሌዎች ከስድስት ወር እስከ አምስት ዓመት ያሉ ሕፃናት " አሳሳቢ " የምግብ እጥረት ላይ እንደሚገኙ የተተደረገው ጥናት አሳይቷል።
በዓለም አቀፍ 'አጣዳፊ የምግብ እጥረት' መለኪያ መሰረት 65 በመቶ የወረዳው ህፃናት በምግብ እጥረት መጎዳታቸውን የጤና ጥበቃ ፅ/ቤቱ መረጃ ያሳያል።
በዚሁ መለኪያ መሠረት 84 በመቶ የወረዳው እናቶችም " በከፋ ደረጃ " የምግብ እጥረት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ዓለሙ በቡግና ወረዳ 7 ሺህ የሚሆኑ ህፃናት በምግብ እጥረት መጎዳታቸውን እና ከ3 ሺህ በላይ ነፍሰ ጡር እናቶችም መጎታዳቸውን አስታውቀዋል።
ለ3 ቀበሌዎች አገልግሎት የሚሰጠው ብርኮ ጤና ጣቢያ ብቻ በኅዳር ወር አራት ሕፃናት በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የጤና ጣቢያ ባለሞያ ተናግረዋል።
በወረዳው በከፍተኛ የምግብ እጥረት የሕፃናት ሕይወት ማለፉን ማረጋገጥ እንዳልቻሉ የተናገሩት አቶ ገ/መስቀል፤ ነገር ግን ሕፃናት "የሞት አፋፍ ላይ" ናቸው ብለዋል።
" የሕክምና ሥርዓቱ ስለፈረሰ ከዚህ በላይ ልየታ ብናደርግ ተጎጂዎች እናገኛለን። . . . እያንዳንዱን ቤት አንኳኩተን አላየነውም " ሲሉ የጤና ቀውሱ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል የአይና ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ መኮንን ገልፀዋል።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል " ለጋሽ ድርጅቶች በአስቸኳይ ወደ ወረዳው ገብተው ማገዝ ካልተቻሉ የሰው ሕይወት እንደሚያልፍ ግልጽ ነው " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ማክሰኞ ታኅሳስ 08/2017 ዓ.ም. ሁለት ተሽከርካሪዎች አልሚ ምግብ እና መድኃኒት ጭነው ቡግና ወረዳ መደረሳቸውን ባለሞያዎች ተናግረዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ ነው።
💠JOIN and Share👇
💠Group:👇
@Ethio_Entrance_discussion
@Ethio_Entrance_discussion
💠Channel:👇
@Ethiopian_Minister_Of_Education