"ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም" 👉ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
ዶ/ር አንዷለም ከስራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ፍትህን በመጠየቅ ላይ ናቸው ሲል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
የዶ/ር አንዷለም ዳኜ ሐዘን በማስመልከት ፍትህ ጥያቄ በተማሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የቀረበበት የሀዘን ምሽት በጥበበ ግዮን ግቢ መካሄዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ፍትህ እንሻለን!፣ ለሃኪሞቻችን ጥበቃ ይደረግልን፤ አዳኙ ፣ አካሚው ሃኪም ለምን ተገደለ፤ አትግደሉን፣ መድሃኒቱ ሃኪም ጥይት አይገባውም የሚሉ መፈክሮችና የፍትህ ጥያቄ አዘል ምልዕክቶች በስራ ባልደረቦቹ፣ በተማሪዎቹ እና በወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መቅረባቸውን ጠቁሟል።
አንድን ትልቅ ሃኪም ቀብሮ ገብቶ ዝም ማለት እንደ ዩኒቨርሲቲ ከብዶናል፡፡ የተገደለብን፣ የተነጠቅነው፣ በርካታ የሆስፒታላችን ደንበኞች ፣ ህሙማን እንዲያድናቸው በወረፋ ቀጠሮ ይዘው የሚጠብቁትን የህዝብ ተስፋ፤ የአገር አንጡራ ሃብት ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችን ሰፊ ሃብት ያፈሰሰችበትን ወጣት ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም ነው፡፡ ፍትህ መጠየቃችንን እንቀጥላለን ብሏል ዩኒቨርሲቲው።
💠JOIN and Share👇
💠Group:👇
@Ethio_Entrance_discussion
@Ethio_Entrance_discussion
💠Channel:👇
@Ethiopian_Minister_Of_Education