የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ቅሬታ!
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የበንሳ ዳዬ ካምፓስ
ባለፈው ሐሙስ ጥር 29/2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ የተገኙ ተፈታኞች፥ "በካምፓሱ በተፈጠረ የኔትወርክ መቋረጥ ምክንያት" ፈተናውን ሳይወስዱ መቅረታቸውን ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡
የመውጫ ፈተናውን መውሰድ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው የካምፓሱን አመራሮች ማነጋገራቸውን፣ ይሁን እንጂ ምንም አይነት መፍትሔ አለማግኘታቸውን ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የበንሳ ዳዬ ካምፓስ ኤክዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑትን ፍሬው ካሳ (ዶ/ር) ጠይቀናል፡፡
በተጠቀሰው ቀን የተሰጠውን የመውጫ ፈተና "በካምፓሱ ሦስት ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች የሆኑ ዘጠኝ ተፈታኞች" አለመውሰዳቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱ ፈተናው መሰጠት ሊጀምር ሲል የኢንተርኔት መቋረጥ መከሰቱንና ችግሩን በቶሎ በመቅረፍ ፈተናውን ለመስጠት ጥረት መደረጉን ፍሬው (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡
ካምፓሱ በሚገኝበት አካባቢ ባለ የመንገድ ሥራ ምክንያት የኢንተርኔት መቋረጥ ማጋጠሙን የገለፁት ኃላፊው፤ ከአካባቢው የኢትዮ ቴሌኮም ቅርንጫፍ ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጋር በመነጋገር ተፈታኞቹ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ጥረት መደረጉንም ገልፀዋል፡፡
የተማሪዎቹን ዕጣፈንታ በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት መደገሩንም አንስተዋል፡፡ በዚህም ያልተፈተኑት ተማሪዎች ዘጠኝ ብቻ በመሆናቸውና ለነሱ ብቻ ሌላ ፈተና ማዘጋጀት የሚቻል ባለመሆኑ፣ ተፈታኞቹ በቀጣይ ሰኔ ወር ላይ ፈተናቸውን እንዲወስዱ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡ ውሳኔው ለተማሪዎቹ እንደተነገራቸውም ኃላፊው ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡
@Exit_Exam_Questions