ኢትዮጵያ ላሙ ወደብን ተጠቅማ ምርቶችን ለማስገባት ተስማምታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሩቶ ገለጹ
ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከየብስ ተከብባ ከምትገኘው ኢትዮጵያ ጋር ወደቡን ወደ ውስጥ ሀገር ለሚገቡ ምርቶች ማጓጓዣነት ለመጠቀም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
የላሙ ወደብ የክልሉ የንግድ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ኬንያ እና ጎረቤት ሀገራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሊደረግበት ተዘጋጅቷል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ በላሙ ምስራቅ ክልል በንዳው ደሴት የመጀመሪያውን የኬንያ ከግሪድ ውጪ የፀሐይ ኃይል ተደራሽነት ፕሮጀክት በሐሙስ ዕለት ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት "ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የላሙን ወደብ መጠቀም ለመጀመር ተስማምተናል፤ ይህም ተጨማሪ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የዚህን ክልል ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያስችለናል" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከሞምባሳ ወደብ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነውን የላሙን ወደብ ላይ የሀገራት መሪዎችን በቅርቡ እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል።በዚህም በላሙ ወደብ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዘመናዊ ማቆሚያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
Via Capital Newspaper
@Ewun_Mereja