ከአዲግራት ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ርዕደ መሬት ተከሰተ
ዛሬ እሁድ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ላይ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው ከቀኑ 5 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ላይ መሆኑንም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰትም፤ በትግራይ ክልል ከተሞች አቅራቢያ ርዕደ መሬት ሲመዘገብ ግን በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ነው። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ቀጠና የተከሰተ መሆኑን የጠቆመው የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC)፤ መጠኑም በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ እንደሆነ አስታውቋል።
በኤርትራ ከአንድ ሳምንት በፊት የደረሰ ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ ተመዝግቧል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በቀይ ባህር ሰሜናዊ አቅጣጫ ከአስመራ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ አካባቢ ነበር። በሀገሪቱ ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽም እንዲሁ ተመሳሳይ ርዕደ መሬት ተመዝግቧል።
በሐምሌ 2015 ዓ.ም. በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተደጋጋሚ ንዝረቶች አስከትሎ እንደነበር ይታወሳል። ንዝረቱን በሽሬ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና መቐለ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች መስማታቸውን በወቅቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸው ነበር።
Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@Ewun_Mereja