የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ትእዛዝ “ አልቀበልም አልፈፅምም “ አለ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ፤ “ በቢሮው ስም የቀረበው መግለጫ የአንድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ አካል ሳይሆን የአንዱ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መሆኑ በግልፅ የሚያሳብቅና የተፈጠረውን ችግር የሚያባብስ ነው “ ብሎታል።
ትናንት መጋቢት 1/2017 ዓ.ም ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮች የጣሉት ጊዚያዊ እግድ ተከትሎ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩት ህወሓት “ እገዳው መሰረተ ቢስ እና የማይተገበር “ በማለት ውድቅ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።
ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጊዚያዊ እግድ ሙሉ በሙሉ በመፃረር ባወጣው መግለጫ ፤ በግልባጭ የተፃፈለትን ትእዘዛዝ እንደማይቀበል በመግለፅ “ የህግ ማስከበር እርምጃው “ ይቀጥላል ብሏል።
@Ewun_Mereja