የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትን እርዳታ ጠየቀ።
የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ዛሬ ረፋድ መግለጫ አውጥቷል።
አስተዳደሩ የትግራይ ጦር አዛዦች ከተልኮ ወጭ የአንድ ጠባብ ቡድን የስልጣን ጥም ለማርካት በማለት ግልፅ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ቆይተዋል ያለ ሲሆን በዚህ ሳምንትም በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ግንባር አዛዦች እንቅስቃሴው በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል ማለቱን በመግለጫው ተመላክቷል።
አስተዳደሩ በመግለጫው ይህንን አደገኛ እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ለአጠቃላይ ጦር አዛዡ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ትእዛዝ ቢሰጥም የጥፋት ድርጊቱ ማስቆም እንዳልቻለ አስታውቋል።
የጥፋት ድርጊቶቹ ተባብሰው በቀጠሉበት በአሁኑ ሰዓት በስቪሎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑንና ከላይ እስከታች ያለውን የመንግስት መዋቅር የማፍረስ እንቅስቃሴዎች ቀጥለዋል ማለቱንም ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው የትግራይ ጦር የበላይ አዛዦች የኃላ ቀሩን ቡዱን ፍላጎት ለማሟላት ሲሉ መንግስት እንዲፈርስ እንዲሁም የፕሪቶርያ ስምምነት በይፋ እንዲጣስ በማድረግ የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እያስገቡት ነውም ብሏል።
አስተዳደሩ በመጨረሻም " የፌደራል መንግስት በትግራይ የፀጥታ ሀይል ስም የሚንቀሳቀሱት አዛዦች የአንድ ኃላቀርና ወንጀለኛ ቡዱን ተላላኪዎች እንጂ የትግራይ ህዝብና ጊዜያዊ አስተዳደሩን እንደማይወክሉ በመረዳት አስፈላጊ እርዳት ማድረግ አለበት" ብሏል። ከዚህ ባሻገር የፕሪቶርያ ስምምነት እንዲ በይፋ ሲፈርስና የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ እልቂት ሲገባ ዝም ብሎ ሊመለከት አይገባም ሲል የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ዛሬ ረፋድ ባወጣው መግለጫ አስታዉቋል።
@Ewun_Mereja