በመቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ተጀመረ
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ለሚመረቁ ተማሪዎች ሞደል የመውጫ ፈተና መስጠት ተጀምሯል፡፡ የመጀመሪያው ዙር ሞዴል የመውጫ ፈተና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ተሰጥቷል፡፡ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የመካነሰላም ግቢ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር መምህር አብዱረህማን አወል እንደገለፁት የሞዴል የመውጫ ፈተናው አላማ ተማሪዎች ለሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ራሳቸውን ያዘጋጁበትን ደረጃ እንዲገመግሙ ከማስቻሉም በላይ በሀገር ደረጃ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በዕውቀትና በክህሎት ላይ ተመስርተው እንዲሰሩ ለማስቻል የሚታዩ እጥረቶችን ለመለየትም ነው ብለዋል፡፡
እንደ መምህር አብዱረህማን ገለፃ ከሞዴል ፈተናው አፈፃፀም በመነሳትም ቴክኖሎጂውን በብቃት ከመጠቀምና የማለፍ ምጣኔን ከማሳደግ አንፃር በቀሪ ጊዜያት በትኩረት የሚሰሩ ስራዎች ተለይተው በሙሉ አቅም የሚሰሩ ይሆናል ፡፡
📄
@Exitnewss
@Exitexamwork